“አእምሩ ከመ ተሰብሐ እግዚአብሔር በጻድቁ”

"እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተመሰገነ እወቁ”

(መዝ.፬፡፫)

በኢ.ኦ.ተ. ቤ/ክ የቦስተን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ።

የቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎቶች

ሥርዓተ ማኅሌት

በከበሮ በጸናጽል የሚደረግ መንፈሳዊ ፡ ምስጋና እና የዜማ ጸሎት ።

ቅዳሴ በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት / የምስጋና ሥርዐት ነው፡፡

ጸሎተ ቅዳሴ ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት ።

1ኛ– «ኦ እኁየ ሀሉ በዝንቱ ልቡና» ከሚለው አንስቶ ሚመጠ ንግርምት” እስከሚለው የዝግጅት ክፍል ፡
2ኛ– «ሚመጠን ግርምት» ከሚለው አንስቶ ፃኡ ንዑሰ ክስቲያን»
እስከሚለው የትምህርት ክፍል ፡

3ኛ– «ፃኡ» ከተባለ በኋላ ያለው ፍሬ ቅዳሴ ነው ፡
የዚህም አፈጻጸም ሥርዓት በሥርዓተ ቅዳሴውና በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 12 በዝርዝር የተመለከተው ነው ።

     ጥምቀት ውሃ በብዛት ከሚፈስበት ጥምቀተ ባሕር በወንዝ ይፈጸማል ። በቤተክርስቲያን ብዛት ያለው ውሃ ካልተገኘ በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ኩሬ በማበጀት ወይም ሰፊ ገንዳ በመሥራት ሰውነትን በሙሉ ሊያጠልቅ በሚችል ውሃ ይፈጸማል ።

     ተጠማቂውን የሚያጠልቅ ውሃ በማይገኝበት ስፍራ የተገኘውን ውሃ ሦስት ጊዜ በእጅ ታፍነው ወይም በጽዋዕ ቀድተው መላ ሰውነቱን እንዲነካው በማድረግ ያጠምቋል ። (ዲድስቅልያ 34። ፍት· ነገሥ· አንቀጽ· 3)።

ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት

           

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው፤ በ፲፩፻፺፯ ዓ.ም ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው «አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡

ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶች

 

ቤተ ክርስቲያን ለሙታን ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግ ታዝዛለች ። ፍትሐት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ የሚለዩት ሰዎች ከማዕሠረ ኃጢአት እንዲፈቱ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ጸሎት ነው ።

ጸሎተ ፍትሐት ሥርየተ ኃጢአትን ፡ ይቅርታን ፡ ዕረፍተ ነፍስን ያሰጣል ። ለደጋጎቹም በክብር ላይ ክብርን ተድላ ዕረፍትን ይጨምራል። ሙታንና ሕያዋን የሚገናኙት በጸሎት አማካይነት ነው። «ሕያዋን ለሙታን ይጸልያሉ ፣ ሙታንም ለሕያዋን ይለምናሉ ። » (ሄኖክ 12፡34) በነፍስ ሕያዋን ናቸውና ፡ (ማቴ 22፡31–32 ፣ ሉቃ· 20፡ 37–39 ። ባሮክ 3:4)

 

በቤተክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት ክርስቲያናዊ ጋብቻ ከመፈጸሙ በፊት የሚከተሉት ግዴታዎች መሟላት አለባቸው ።

  • ጸጋ መንፈስ ቅዱስን በእኩልነት የሚቀበሉ ስለሆኑ ሁሉም ክርስቲያን መሆን አለባቸው ።
  • ሁለቱም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባላት መሆን አለባቸው።
  • ሁለቱ አንድ ካልሆኑ ግን ጋብቻው ከመፈጸሙ በፊት የቤተክርስቲያናችን አባል መሆን ግዴታ ነው ።
  • ከጋብቻ በፊት ሥጋዊ ግንኙነት አይፈቀድም ።
  • ለጋብቻው ሁለቱም ፈቃደኞች መሆን አለባቸው ።
  • በቤተሰብ መካከል የሥጋዊም ሆነ የመንፈሳዊ ተዘምዶ ገደብ በጋብቻ እንዳይፈርስ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ መከበር አለበት

የሕጻናት እና የሰንበት ት/ቤት

  • የአማርኛ ፊደል ፣ ቁጥር ፣ ንባብ እና ጽሁፍ ጥናት
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ
  • የወረብ እና መዝሙር ጥናት በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ
  • ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ
  • ተከታታይ ትምህርተ ሃይማኖት በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ
  • የአብነት ትምህርት በግዕዝ (ጸሎተ ሃይማኖት ፣ ውዳሴ ማርያም ፣ መልክዐ መልክዕ ፣ ሥርዓተ ቅዳሴ ፣ ዳዊት … ወዘተ ንባብ እና ዜማ)
  • መንፈሳዊ ድራማዎችንና እንዲሁም ሌሎች ዝግጅቶችን ለምዕመናን ማቅረብ

የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት ለማገዝ ፈቃደኛ ከሆናችሁ።

« ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር » 

መዝ ፤ ፻፲፭፣ ፯

« የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው »

መዝ ፤ 115(116):15

መንፈሳዊ አገልግሎቶች እና የአገልግሎት ጊዜያት
ጸሎተ ነግሕ4:30am
የሰንበት ቅዳሴ6:00am
የሰንበት ት/ቤት መዘምራን መዝሙር8:45am
የወንጌል ትምሕርት9:00am
ያግኙን
ማህበራዊ ገጾች
አድራሻ