ውዳሴሃ ፡ ለእግዝእትነ ፣ ማርያም ፡ ድንግል ፡ ወላ ዲተ ፡ አምላክ ፡ ዘይትነበብ ፡ በዕለተ ፡ ሰኑይ ።

 

ፈቀደ እግዚእ ያግእዞ ለአዳም
ኅዙነ ወትኩዘ ልብ ወያግብኦ ሀበ
ዘትካት መንበሩ ሰኣሊ ለነ
ቅድስት፡፡

ሠረቀ በሥጋ እምድንግል
ዘእንበለ ዘርአ ብእሲ ወአድኅነነ፡፡
ለሔዋን እንተ አስረታ ከይሲ
ፈትሐ ላእሌሃ እግዚአብሔር
እንዘ ይብል ብዙኅ አበዝኖ
ለሕማምኪ ወለፃዕርኪ ሠምረ
ልቡ ኀበ ፍቅረ ሰብእ ወአግዓዛ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ዘተሰብአ
ወኀደረ ላዕሌነ ወርኢነ ስብሐቲሁ
ከመ ስብሐተ አሐዱ፡፡ ዋሕድ
ለአቡሁ ሰምረ ይሣሃለነ፡፡ ሰኣሊ
ለነ ቅድስት፡፡

ርእየ ኢሳይያስ ነቢይ በመንፈሰ
ትንቢት ምሥጢሮ ለአማኑኤል
ወበእንተዝ ጸርሐ እንዘ ይብል
ሕፃን ተወልደ ለነ ወልድ ተውህበ
ለነ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

ተፈሣሕ ወተሐሠይ ኦ ዘመደ
ዕጓለ እመሕያው እስመ አፍቅሮ
እግዚአብሔር ለዓለመ ወመጠወ
ወልዶ ዋህደ ከመ ይሕያው ኲሉ
ዘየኣምን ቦቱ እስከ ለዓለም ፈነወ
ለነ መዝራዕቶ ልዑለ፡፡ ሰአሊ ለነ
ቅድስት

ዘሀሎ ወይሄሉ ዘመጽአ ወካዕበ
ይመጽእ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል
ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበላ ውላጤ
ኮነ ፍጹመ ሰብእ ኢትበዐደ
ወኢተፈልጠ በኲሉ ግብሩ ወልድ
ዋህድ አላ አሐዱ ራእይ ወአሐዱ
ህላዌ ወአሐዱ መለኮት
ዘእግዚአብሔር ቃል፡፡ ሰኣሊ ለነ
ቅድስት፡፡

ተፈሥሒ ኦ ቤተ ልሔም
ሀገሮሙ ለነቢያት እስመ በኀቤኪ
ተወልደ ክርስቶስ ዳግማይ አዳም
ከመ ያግብኦ ለአዳም ቀዳሚ
ብእሲ እምድር ውስተ ገነት
ይስዐር ፍትሐ ሞት ኦ ኣዳም
መሬት አንተ ወትገብእ ውስተ
መሬት፡፡ ኀበ ሀለወት ብዝኅት
ኃጢአት በህየ ትበዝኅ ጸጋ
እግዚአብሔር፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት

ትትፌሣሕ ወትትሐሠይ ኵሉ
ነፍስተ ሰብእ ምስለ መላእክት
ይሴብሕዎ ለክርስቶስ ንጉሥ
ይጸርሑ ወይብሉ ስብሐት
ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም
በምድር ሥምረቱ ለሰብእ እስመ
ዕፀረ ዘትካት ወነሠተ ምክሮ
ለጸላዒ ወሠጠጠ መጽሐፈ
ዕዳሆሙ ለአዳም ወለሔዋን
ወረሰዮሙ ኣግዓዝያነ ዘተወልደ
ስነ በሀገረ ዳዊት መድኃኒነ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰአሊ ለነ
ቅድስት፡፡

ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኩሉ
ሰብእ ለእለ ይነብሩ ውስተ ዓለም
በእንተ ፍቅረ ሰብእ መጻእከ
ውስተ ዓለም ወኵሉ ፍጥረት
ተፈሥሐ በምጽአትከ፡፡ እስመ
አድኀንኮ ለአዳም እምስሕተት
ወረሰይካ ለሔዋን ኣግዓዚተ
እምጻዕረ ሞት ወወሀብከነ.
መንፈስ ልደት፡፡ ባረክናከ ምስለ
መላእክቲካ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

1. ጌታ ልቡ ያዘነና የተከዘ
አዳምን ነጻ ያወጣውና ወደ ቀድሞ ቦታው ይመልሰው ዘንድ ወደደ ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ፡፡

2. ከድንግል ያለ ወንድ ዘር በሥጋ ተወለደና ኣዳነን፡፡
ከይሲ ዲያቢሎስ ያሳታት ሔዋንን እግዚአብሔር
ምጥሽንና ጻርሽን አበዛዋለሁ ብሎ ፈረደባት፡፡
ሰውን ወደደና ነፃ አደረጋት፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

3. ሰው የሆነና በኛ ያደረ ቃል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ክብሩንም ለአባቱ አንድ እንደመሆኑ ክብር አየነ፡፡
ይቅር ይለን ዘንድ ወደደ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

4. ነቢዩ ኢሳይያስ በመንፈስ ቅዱስ የዐማኑኤልን ምስጠር አየ፡፡ ስለዚህም ሕፃን ተወለደልን፤ ወልድም ተሰጠልን ብሎ አሰምቶ ተናገረ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

5. ሰው ሆይ ፈጽመህ ደስ ይበልህ፤ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና፤ አንድ ልጁንም የሚያምንበት ሁሉ እስከ ዘለዓለም ፈጽሞ ይድን ዘንድ አሳልፎ ሰጥቷልና፡፡ ልዑል ክንዱን ሰደደልን፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

6. የነበረው የሚኖረው፤ የመጣው ዳግመኛ የሚመጣውም ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ያለመለወጥ ፍጹም ሰው ሆነ፡፡ አንዱ ወልድ በሥራው ሁሉ አልተለየም፣ የእግዚአብሔር መለኮት አንድ ነው እንጂ፤ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

7. የነቢያት ሀገራቸው ቤተ ልሔም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ በአንቺ ዘንድ ተወልዷልና፤ የቀድሞውን ሰው አዳምን ከምድር /ከሲኦል/ ወደ ገነት ይመልሰው ዘንድ፡፡ አዳም ሆይ መሬት ነበርህና ወደ መሬት ትመለሳለህ ብሎ የፈረደበትንም የሞት ፍርድ ያጠፋለት ዘንድ፡፡ ብዙ ኃጢአት ባለችበት የእግዚኣብሔር ጸጋ ትበዛለች፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

8. የሰው ሁሉ ሰውነት ደስ ይላታል፡፡ በሰማይ ለእግዚኣብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰውም እርሱ በሚፈቅደው እያሉ ኣሰምተው ንጉሥ ክርስቶስን ከመላእክት ጋራ ያመሰግኑታል፤ የቀድሞውን እርግማን አጥፍቷልና፡፡ የጠላትን ምክሩን አፈረሰበት፡፡ ለአዳምና ለሔዋን የዕዳ ደብዳቤያቸውን ቀደደላቸው ፥ በዳዊት ሀገር የተወለደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምንና ሔዋንን ነፃ አደረጋቸው፤ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

9. በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታበራ እውነተኛ ብርሃን ስለ ሰው ፍቅር ወደ ዓለም የመጣህ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በመምጣትህ ደስ አለው፥ አዳምን ከስሕተት አድነኸዋልና ሔዋንንም ከሞት ጻዕረኝነት ነፃ አድርገኻታልና፡፡ የምንወለድበትን መንፈስ በረቂቁን ልደት ሰጠኸን፥ ከመላእክት ጋርም አመሰገንህ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

 

1. God wished to set free ADAM, Who was sad at heart and
sorrowful, and in the greatness of His compassion and mercy to
bring him back to the state wherein he was formerly.

2. He rose up in flesh of the Virgin without the seed of man. He
came, He saved us. God passed the decree of judgment upon EVE
whom the serpent led astray, saying, “I will multiply greatly thy
pain and thy suffering” (Genesis iii. 16). Nevertheless, His heart
inclined to love for man, and He set him free. He hath appeared.

3. JESUS CHRIST, the Word Who became incarnate, and He
dwelt with us, and we saw His glory like the glory of the Only
begotten of His Father (John i.14), He hath been pleased to show
compassion upon us. He hath appeared.

4. ISAIAH the Prophet in the spirit of prophecy saw the mystery
of EMMANUEL, and therefore he cried out, saying, “A Child is
born unto us, a Son is given unto us” (Isaiah ix. 6). He hath
appeared.

5. Rejoice and be glad, O race of the children of men, for God
hath loved the world, and given His only Son that all who
believes in Him may have everlasting life (John iii. 16). The Most
High hath sent unto us His arm. He hath appeared.
6. He Who was and shall be, He Who came and shall come
again, is JESUS CHRIST, the Word Who became incarnate
without any change. He was a perfect man, without division and
without separation, in all His work the only begotten, but with
one form, one being, and one divinity (or, Godhead)—God the
Word. He hath appeared.

7. Rejoice, O BETHLEHEM, the town of the Prophets, for in
thee was born CHRIST, the second ADAM, so that He might
bring the first ADAM from the earth into the Garden (i.e.
Paradise), and destroy the doom of death. O ADAM, dust thou art
and to dust shalt thou return. Where sin abounded there the grace
of God abounded likewise (Romans v.20). He hath appeared.
8. Let all souls of men rejoice and be glad with the angles, and let
them praise CHRIST, the Kind, and cry out and say, “Glory to
God in the heavens, and peace on the earth, [and] His good will to
men” (Luke ii. 14). He hath abolished the things of old, and
overthrown the plot of the Enemy, and torn in pieces the bill of
indictment (Ephesians ii. 15) of ADAM and EVE and set them
free, –He Who was born for us in the city of DAVID our
Redeemer, JESUS CHRIST hath done this. He hath appeared.

9. Thou Light, Who in truth illuminest all men who dwell in the
world, because of Thy love for man Thou hast come into the
world, because of Thy love for man Thou hast come into the
world. All created things rejoiced at Thy coming, because Thou
didst deliver ADAM from his error, anddidst set free EVE from
the suffering of death, and hast given unto us the soul of
prophecy. We bless Thee with Thine angles. [Rubric]. On fast
days thou shalt say thus; CHRIST hath risen up in the flesh of the
Virgin: He fasted forty days and forty nights in order that He
might deliver us.

 

ፈቀደ እግዚእ ያግእዞ ለአዳም
ኅዙነ ወትኩዘ ልብ ወያግብኦ ሀበ
ዘትካት መንበሩ ሰኣሊ ለነ
ቅድስት፡፡

ሠረቀ በሥጋ እምድንግል
ዘእንበለ ዘርአ ብእሲ ወአድኅነነ፡፡
ለሔዋን እንተ አስረታ ከይሲ
ፈትሐ ላእሌሃ እግዚአብሔር
እንዘ ይብል ብዙኅ አበዝኖ
ለሕማምኪ ወለፃዕርኪ ሠምረ
ልቡ ኀበ ፍቅረ ሰብእ ወአግዓዛ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ዘተሰብአ
ወኀደረ ላዕሌነ ወርኢነ ስብሐቲሁ
ከመ ስብሐተ አሐዱ፡፡ ዋሕድ
ለአቡሁ ሰምረ ይሣሃለነ፡፡ ሰኣሊ
ለነ ቅድስት፡፡

ርእየ ኢሳይያስ ነቢይ በመንፈሰ
ትንቢት ምሥጢሮ ለአማኑኤል
ወበእንተዝ ጸርሐ እንዘ ይብል
ሕፃን ተወልደ ለነ ወልድ ተውህበ
ለነ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

ተፈሣሕ ወተሐሠይ ኦ ዘመደ
ዕጓለ እመሕያው እስመ አፍቅሮ
እግዚአብሔር ለዓለመ ወመጠወ
ወልዶ ዋህደ ከመ ይሕያው ኲሉ
ዘየኣምን ቦቱ እስከ ለዓለም ፈነወ
ለነ መዝራዕቶ ልዑለ፡፡ ሰአሊ ለነ
ቅድስት

ዘሀሎ ወይሄሉ ዘመጽአ ወካዕበ
ይመጽእ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል
ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበላ ውላጤ
ኮነ ፍጹመ ሰብእ ኢትበዐደ
ወኢተፈልጠ በኲሉ ግብሩ ወልድ
ዋህድ አላ አሐዱ ራእይ ወአሐዱ
ህላዌ ወአሐዱ መለኮት
ዘእግዚአብሔር ቃል፡፡ ሰኣሊ ለነ
ቅድስት፡፡

ተፈሥሒ ኦ ቤተ ልሔም
ሀገሮሙ ለነቢያት እስመ በኀቤኪ
ተወልደ ክርስቶስ ዳግማይ አዳም
ከመ ያግብኦ ለአዳም ቀዳሚ
ብእሲ እምድር ውስተ ገነት
ይስዐር ፍትሐ ሞት ኦ ኣዳም
መሬት አንተ ወትገብእ ውስተ
መሬት፡፡ ኀበ ሀለወት ብዝኅት
ኃጢአት በህየ ትበዝኅ ጸጋ
እግዚአብሔር፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት

ትትፌሣሕ ወትትሐሠይ ኵሉ
ነፍስተ ሰብእ ምስለ መላእክት
ይሴብሕዎ ለክርስቶስ ንጉሥ
ይጸርሑ ወይብሉ ስብሐት
ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም
በምድር ሥምረቱ ለሰብእ እስመ
ዕፀረ ዘትካት ወነሠተ ምክሮ
ለጸላዒ ወሠጠጠ መጽሐፈ
ዕዳሆሙ ለአዳም ወለሔዋን
ወረሰዮሙ ኣግዓዝያነ ዘተወልደ
ስነ በሀገረ ዳዊት መድኃኒነ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰአሊ ለነ
ቅድስት፡፡

ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኩሉ
ሰብእ ለእለ ይነብሩ ውስተ ዓለም
በእንተ ፍቅረ ሰብእ መጻእከ
ውስተ ዓለም ወኵሉ ፍጥረት
ተፈሥሐ በምጽአትከ፡፡ እስመ
አድኀንኮ ለአዳም እምስሕተት
ወረሰይካ ለሔዋን ኣግዓዚተ
እምጻዕረ ሞት ወወሀብከነ.
መንፈስ ልደት፡፡ ባረክናከ ምስለ
መላእክቲካ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

 

1. ጌታ ልቡ ያዘነና የተከዘ
አዳምን ነጻ ያወጣውና ወደ ቀድሞ ቦታው ይመልሰው ዘንድ ወደደ ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ፡፡

2. ከድንግል ያለ ወንድ ዘር በሥጋ ተወለደና ኣዳነን፡፡
ከይሲ ዲያቢሎስ ያሳታት ሔዋንን እግዚአብሔር
ምጥሽንና ጻርሽን አበዛዋለሁ ብሎ ፈረደባት፡፡
ሰውን ወደደና ነፃ አደረጋት፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

3. ሰው የሆነና በኛ ያደረ ቃል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ክብሩንም ለአባቱ አንድ እንደመሆኑ ክብር አየነ፡፡
ይቅር ይለን ዘንድ ወደደ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

4. ነቢዩ ኢሳይያስ በመንፈስ ቅዱስ የዐማኑኤልን ምስጠር አየ፡፡ ስለዚህም ሕፃን ተወለደልን፤ ወልድም ተሰጠልን ብሎ አሰምቶ ተናገረ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

5. ሰው ሆይ ፈጽመህ ደስ ይበልህ፤ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና፤ አንድ ልጁንም የሚያምንበት ሁሉ እስከ ዘለዓለም ፈጽሞ ይድን ዘንድ አሳልፎ ሰጥቷልና፡፡ ልዑል ክንዱን ሰደደልን፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

6. የነበረው የሚኖረው፤ የመጣው ዳግመኛ የሚመጣውም ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ያለመለወጥ ፍጹም ሰው ሆነ፡፡ አንዱ ወልድ በሥራው ሁሉ አልተለየም፣ የእግዚአብሔር መለኮት አንድ ነው እንጂ፤ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

7. የነቢያት ሀገራቸው ቤተ ልሔም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ በአንቺ ዘንድ ተወልዷልና፤ የቀድሞውን ሰው አዳምን ከምድር /ከሲኦል/ ወደ ገነት ይመልሰው ዘንድ፡፡ አዳም ሆይ መሬት ነበርህና ወደ መሬት ትመለሳለህ ብሎ የፈረደበትንም የሞት ፍርድ ያጠፋለት ዘንድ፡፡ ብዙ ኃጢአት ባለችበት የእግዚኣብሔር ጸጋ ትበዛለች፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

8. የሰው ሁሉ ሰውነት ደስ ይላታል፡፡ በሰማይ ለእግዚኣብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰውም እርሱ በሚፈቅደው እያሉ ኣሰምተው ንጉሥ ክርስቶስን ከመላእክት ጋራ ያመሰግኑታል፤ የቀድሞውን እርግማን አጥፍቷልና፡፡ የጠላትን ምክሩን አፈረሰበት፡፡ ለአዳምና ለሔዋን የዕዳ ደብዳቤያቸውን ቀደደላቸው ፥ በዳዊት ሀገር የተወለደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምንና ሔዋንን ነፃ አደረጋቸው፤ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

9. በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታበራ እውነተኛ ብርሃን ስለ ሰው ፍቅር ወደ ዓለም የመጣህ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በመምጣትህ ደስ አለው፥ አዳምን ከስሕተት አድነኸዋልና ሔዋንንም ከሞት ጻዕረኝነት ነፃ አድርገኻታልና፡፡ የምንወለድበትን መንፈስ በረቂቁን ልደት ሰጠኸን፥ ከመላእክት ጋርም አመሰገንህ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

 

1. God wished to set free ADAM, Who was sad at heart and
sorrowful, and in the greatness of His compassion and mercy to
bring him back to the state wherein he was formerly.

2. He rose up in flesh of the Virgin without the seed of man. He
came, He saved us. God passed the decree of judgment upon EVE
whom the serpent led astray, saying, “I will multiply greatly thy
pain and thy suffering” (Genesis iii. 16). Nevertheless, His heart
inclined to love for man, and He set him free. He hath appeared.

3. JESUS CHRIST, the Word Who became incarnate, and He
dwelt with us, and we saw His glory like the glory of the Only
begotten of His Father (John i.14), He hath been pleased to show
compassion upon us. He hath appeared.

4. ISAIAH the Prophet in the spirit of prophecy saw the mystery
of EMMANUEL, and therefore he cried out, saying, “A Child is
born unto us, a Son is given unto us” (Isaiah ix. 6). He hath
appeared.

5. Rejoice and be glad, O race of the children of men, for God
hath loved the world, and given His only Son that all who
believes in Him may have everlasting life (John iii. 16). The Most
High hath sent unto us His arm. He hath appeared.
6. He Who was and shall be, He Who came and shall come
again, is JESUS CHRIST, the Word Who became incarnate
without any change. He was a perfect man, without division and
without separation, in all His work the only begotten, but with
one form, one being, and one divinity (or, Godhead)—God the
Word. He hath appeared.

7. Rejoice, O BETHLEHEM, the town of the Prophets, for in
thee was born CHRIST, the second ADAM, so that He might
bring the first ADAM from the earth into the Garden (i.e.
Paradise), and destroy the doom of death. O ADAM, dust thou art
and to dust shalt thou return. Where sin abounded there the grace
of God abounded likewise (Romans v.20). He hath appeared.
8. Let all souls of men rejoice and be glad with the angles, and let
them praise CHRIST, the Kind, and cry out and say, “Glory to
God in the heavens, and peace on the earth, [and] His good will to
men” (Luke ii. 14). He hath abolished the things of old, and
overthrown the plot of the Enemy, and torn in pieces the bill of
indictment (Ephesians ii. 15) of ADAM and EVE and set them
free, –He Who was born for us in the city of DAVID our
Redeemer, JESUS CHRIST hath done this. He hath appeared.

9. Thou Light, Who in truth illuminest all men who dwell in the
world, because of Thy love for man Thou hast come into the
world, because of Thy love for man Thou hast come into the
world. All created things rejoiced at Thy coming, because Thou
didst deliver ADAM from his error, anddidst set free EVE from
the suffering of death, and hast given unto us the soul of
prophecy. We bless Thee with Thine angles. [Rubric]. On fast
days thou shalt say thus; CHRIST hath risen up in the flesh of the
Virgin: He fasted forty days and forty nights in order that He
might deliver us.

1. አክሊለ ምክሕነ ወቀዳሚተ መድኃኒትነ ወመሠረተ ንጽሕነ ኮነ በማርያም ድንግል እንተ ወለደት ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ ዘኮነ ሰብአ በእንተ መድኃኒትነ፡፡ እምድኅረ ኮነ ሰብአ ጥዩቀ አምላክ ፍጹም ውእቱ ወበእንተዝ ወለደቶ እንዘ ድንግል ይእቲ፡፡ መንክር ኃይለ ወሊዶታ ዘኢይትነገር፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

2. እስመ በፈቃዱ ወበሥምረተ አቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ መጽአ ወአድኅነነ፡፡ ዐቢይ ውእቱ ስብሐተ ድንግልናኪ ኦ ማርያም ድንግል ፍጽምት ረከብኪ ሞገሰ እግዚአብሔር ምስሌኪ አንቲ ውእቱ ሰዋስው ዘርእየ ያዕቆብ እምድር ዘይበጽሕ እስከ ሰማይ ወመላእክተ እግዚአብሔር የዐርጉ ወይወርዱ ውስቴታ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

3. አንቲ ውእቱ ዕፅ ዘርእየ ሙሴ በነደ እሳት ወኢትውዒ፡፡ ዘውእቱ ወልደ እግዚአብሔር መጽኣ ወኃደረ ውስተ ከርሥኪ ወእሳተ መለኮቱ ኢያውዓየ ሥጋኪ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

4. አንቲ ውእቱ ገራህት ዘኢተዘርአ ውስቴታ ዘርእ ወጽአ እምኔኪ ፍሬ ሕይወት፡፡ አንቲ ውእቱ መዝገብ ዘተሣየጠ ዮሴፍ ወረከበ በውስቴታ ባሕርየ ዕንቈ ክቡረ ዘውእቱ መድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተጸውረ በከርሥኪ ወወለድኪዮ ውስተ ዓለም፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

5. ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ እግዚእ ኃሤቶሙ ለመላእክት ተፈሥኢ ኦ ንጽሕት ዜናሆሙ ለነቢያት፡፡ ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገሰ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡፡ ተፈሥሒ እስመ ተወከፍኪ ቃሎ ለመልአክ ፍሥሐ ኵሉ ዓለም፡፡ ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ ፈጣሬ ኵሉ ዓለም፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

6. ተፈሥሒ እስመ ድልወ ተሰመይኪ ኦ ወላዲተ አምላክ፡፡ ተፈሥሒ ኦ መድኃኒታ ለሔዋን፡፡ ተፈሥሒ እንተ አጥበውኪ ሐሊበ ለዘይሴስዮ ለኵሉ ፍጥረት፡፡ ተፈሥሒ ኦ ቅድስት እሞሙ ለኵሎሙ ሕያዋን ናንቀዐዱ ኀቤኪ ትስአሊ በእንቲአነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

7. ኦ ድንግል ኦ ቅድስት ኦ ወላዲተ እግዚእ እስመ ወለድኪ ለነንጉሠ መንክር ምሥጢር ኀደረ ላዕሌኪ ለመድኃኒተ ዚአነ ናርምም እስመ ኢንክል ፈጽሞ ጥንቁቀ ነጊረ በእንተ ዕበዩ ለውእቱ ገባሬ ሠናያት በብዙኅ መንክር ራእይ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

8. ቃለ አብ ሕያው ዘወረደ ውስተ ደብረ ሲና፡፡ ወወሀበ ሕገ ለሙሴ ወከደነ ርእሰ ደብር በጊሜ ወጢስ በጽልመት ወነፋስ ወበድምፀ ቃለ አቅርንት ይጌሥፅ ለእለ ይቀውሙ በፍርሃት፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

9. ውእቱኬ ዘወረደ ኀቤኪ ኦ ደብር ነባቢት በትሕትና መፍቀሬ ሰብእ ተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ውላጤ ፍጹመ ሥጋ ነባቢ ዘከማነ በመንፈሰ ጥበብ አምላክ ኀደረ ላዕሌሃ ኮነ ፍጸመ ሰብአ ከመ ያድኅኖ ወይሥረይ ኃጢአቶ ለአዳም፡፡ ወያንብሮ ውስተ ሰማያት ወያግብኦ ኀበ ዘትካት መንበሩ በዕበየ ሣህሉ ወምሕረቱ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

10. ዕበያ ለድንግል ኢይትከሃል ለተነግሮ፡፡ እስመ እግዚእ ኀረያ፡፡ መጽኣ ወኀደረ ላዕሌሃ ዘየኀድር ውስተ ብርሃን ኀበ አልቦ ዘይቀርቦ፡፡ ተጸውረ በከርሣ ፱ተ አውራኃ ዘኢይትረአይ ወዘኢይትዐወቅ፡፡ ወለደቶ ማርያም እንዘ ድንግል ይእቲ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

11. ዘውእቱ ዕብን ዘርእየ ዳንኤል ነቢይ ዘተበትከ፡፡ እምደብር ነዋኅ ዘእንበለ እድ ዘውእቱ ቃል ዘወጽአ እምኀበ አብ መጽአ ወተሰብአ እምድንግል ዘእንበለ ዘርአ ብእሲ ወአድኅነነ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

12. ኮንኪ አጽቀ ንጹሐ ወሙዳየ አሚን፡፡ ርትዕት ሃይማኖቶሙ ለቅዱሳን አበዊነ፡፡ ኦ ንጽሕት ወላዲተ አምላክ ድንግል ኅትምት ወለድኪ ለነ ቃለ አብ ኢየሱስ ክርስቶስ መጽአ ለመድኃኒትነ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

13. አንቲ እሙ ለብርሃን ክብርት ወላዲተ እግዚእ እንተ ፆርኪዮ ለቃል ዘኢይትረአይ፡፡ እምድኅረ ወለድኪ ኪያሁ ነበርኪ በድንግልና፡፡ በስብሐት ወበባርኮት ያዐብዩኪ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

14. አይ ልሳን ዘይክል ነቢበ ዘይትናገር በእንቲአኪ ኦ ድንግል ንጽሕት እሙ ለቃለ ኣብ፡፡ ኮንኪ መንበሮ ለንጉሥ ለዘይፀውርዎ ኪሩቤል፡፡ ናስተበፅዐኪ ኦ ቡርክት ወንዘክር ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ፡፡ ኦ ርግብ ሠናይት እሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

15. ተፈሥሒ ኦ ማርያም እም ወአመት፡፡ እስመ ለዘውስተ ሕፅንኪ ይሴብሕዎ መላእክት ወኪሩቤል ይሰግዱ ሎቱ በፍርሀት፤ ወሱራፌል ዘእንበለ ጽርኣት፡፡ ይሰፍሑ ክነፊሆሙ፡፡ ወይብሉ ዝንቱ ውእቱ ንጉሠ ስብሐት፡፡ መጽአ ይሥረይ ኃጢአተ ዓለም በዕበየ ሣህሉ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

1. የመመኪያችን ዘውድ የድኀነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት ስለማዳን ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል በወለደችልን ሰድንግል ማርያም ተገኘልን ሰው ከሆነ በኋላም ፍጹም አምላክ ነው ስለዚህም በድንግልና ወለደችው፡፡ ድንቅ የሆነ የመውለድዋ ችሎታ የማይመረመር ሊነገር የማይቻል ነው:: ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

2. በእርሱ ፈቃድ በአባቱ ፈቃድ ሰመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ መጥቶ ኣዳነን፡፡ በድንግልና ፍጽምት የሆንሽ ማርያም ሆይ የድንግልናሽ ምሥጋናና ክብር ታላቅ ነው እግዚኣብሔር ካንቺ ጋር ሲሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና ያዕቆብ ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያያት መሰላል አንቺ ነሽ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

3. ሙሴ በነደ እሳት ሳትቃጠል ያያት ዕፅ አንቺ ነሽ ይኸውም መጥቶ በማኀፀንሽ ያደረው የእግዚአብሔር ነው የመስኮቱ እሳትነት ሥጋሽን አላቃጠለውም። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

4. ዘር ያልተዘራባት እርሻ አንቺነሽ የሕይወት ፍሬ ከአንቺ ወጣ፡፡ ዮሴፍ የዋጃትና የከበረ ዕንቁን ያገኘባት ሣጥን አንቺ ነሽ ይኸውም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በማኀፀንሽ ኣደረ በዚህ ዓለምም ወስድሽው ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

5. የመላእክት ደስታቸው የሆነ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ የነቢያት ዜናቸው ንጽሕት ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ሲሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ:: የዓለም የሰው ሁሉ ደስታ የሆነ የመልአኩን ቃል ተቀብለሻልና ደስ ይበልሽ:: ዓለምን ሁሉ የፈጠረ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

6. በሚገባ የአምላክ እናት ተብለሻልና ደስ ይበልሽ፡፡ የሔዋን መድኃኒት ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግበውን እሱን ጡትሽን አጥብተሽዋልና ደስ ይበልሽ፡፡ የሕያዋን የጻድቃን ሁሉ እናታቸው ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ትለምኝልን ዘንድ ወደ አንቺ እናንጋጥጣለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

7.ድንግል ሆይ ቅድስት ሆይ ጌታን የወለድሽ ሆይ እኛን ለማዳን ድንቅ ምሥጢር (ተዋህዶ) በአንቺ ሲደረግ ንጉሥን ወልደሽልናልና ፍጥረታትን በልዩ ልዩ መልክ የፈጠረ የርሱን የገናንነቱን ነገር ፈጽመን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

8. ወደ ደብረሲና የወረደ ለሙሴ ሕግን የሰጠ የተራራውን እራስ በጽጋግ በጢስ በጨለማና በነፋስ የሸፈነ ፈርተው የቆሙትንም በነጋሪቶች ደምጽ የገሠፀ የአብ አካላዊ ቃል ነው፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

9. በትሕትና የተናገርሽ ተራራ ሆይ ይኸውም ወደ አንቺ የወረደው ነው ሰውን የወደደ እርሱ ያለመለወጥ ባንቺ ሰው ሆነ እንደ እኛ በሚናገር ሥጋ ፍጹም ሆኖ አምላክ በመንፈስ ቅዱስ በማኅፀኗ አደረና ፍጹም ሰው ሆነ አዳምን ያድነው ዘንድ ኀጢአቱንም ያስተሠርይለት ዘኝድ በሰማያት በሰማያዊ መዓረግ ያኖረው በዘንድ በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት ወደ ቦታው ይመልሰው ዘንድ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

10. የድንግልን ገናንነቷን ሊናገሩት አይቻልም፡፡ ጌታ መርጧታልና የሚቀርበው ስሌለ ብርሃኝ ውስጥ የሚኖር እርሱ መጥቶ አደረባት ዘጠኝ ወር ሰማኀፀንዋ ኣደረ የማይታይና የማይመረመር ታይቶ የማይታወቅ እርሱን በድንግልና ወለደችው ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

11. ነቢዩ ዳንኤል ያየው ያለ እጅ ከረጅም ተራራ የተፈነቀለው ያ ደንጊያ ከአብ ዘንድ የወጣው ቃል ነውና መጥቶ ያለ ወንድ ዘር ከድንግል ተወልዶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

12. እንደ ንጹሕ ጫፍ ሆንሽ የሃይማኖት መገኛ የቀናች የቅዱሳን ኣባቶቻችን ሃይማኖታቸው ኣምላክን የወለድሽና ሰድንግልና የታተምሽ ንጽሕት ሆይ የአብን ቃል ወለድሽልን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን መጣ ቅድስት ለምኝልን፡፡

13. የከበርሽ ጌታን የወለድሽ ሆይ የማይታይ ቃልን የተሸከምሽው የብርሃን እናቱ አንቺ ነሽ እሱን ካወለደሽው በኋላ በድንግልና ኖረሳልና በፍጹም ምስጋና ያገኑሻል ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

14. የአብ ቃል እናቱ ንጽሕት ድንግል ሆይ ስለአንቺ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው ኪሩቤል ለሚሸከሙት ንጉሥ ዙፋኑ (ማደሪያው) ሆንሽ የተከበርሽ ሆይ እናመሰግንሻለን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ መልካሟ እርግብ ሆይ ስምሽን ለልጅ ልጅ እንጠራለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

15. እናትና ገረድ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ የታቀፍሽውን መላእክት ያመሰግኑታልና ኪሩቤልም በፍርሃት ይሰግዱለታል ሱራፌልም ያለማቋረጥ ክንፋቸውን ዘርግተው የሚያመስግኑት ንጉሥ የክብር ባለቤት ይህ ነው በይቅርታው ብዛት የዓለምን ኃጢአት ያስተሠርይ ዘንድ የመጣው ይህ ነው ይላሉ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

1. The crown of our glory and the origin of our deliverance (or,
salvation) and the foundation of our sanctification came into
being in MARY the Virgin, who brought for us God the Word,
Who became incarnate for our salvation. And after He became
man of a certainty He was perfect God. And for this reason she
gave birth to Him being a virgin. The power of her bringing
forth is a marvellous thing that cannot be described. Of His own
free will, and by the good pleasure of His Father and the Holy
Spirit, He came forth and hath delivered us.

2. Great is the praise of thy virginity, O MARY, thou perfect
(or, absolute) virgin. Thou didst receive grace, God was with
thee. Thou art the Ladder which JACOB saw reaching from
earth to heaven, with the angles of God ascending and
descending upon it (Genesis xxviii. 12). So then

3. Thou art the Bush which MOSES saw blazing with fire, and
the wood thereof was not consumed (Exodus iii.2). It was the
son of God Who dwelt in thy womb, and the fire of His divinity
did not consume thy flesh. So then

4. Thou art that Field wherein no seed was sown, and yet there
went forth from thee the Fruit of Life. Thou art that Treasurehouse
which JOSEPH bought, and he found therein a Pearl, a
precious gem, that is to say, or Redeemer JESUS CHRIST. Thou didst
carry it in thy womb and didst bring Him forth into the world.
So then

5. Rejoice thou, O God bearer, thou joy of the angels. Rejoice
thou, who wast the woman foretold by the Prophets. Rejoice
thou, for thou didst find favour, God was with thee. Rejoice
thou, for thou hast received the voice of the Angel [GABRIEL],
the joy of all the world. Rejoice thou, O Bearer of the Creator
of all the world. So then

6. Rejoice thou because it is meet that thou shouldst be called,
“Bearer of God”. Rejoice thou, O thou woman who deliveredst
EVE. Rejoice thou, for thou didst suckle Him Who suckleth all
creation. Rejoice thou, O holy woman, the mother of all living
beings. We lift our eyes to thee with entreaty that thou wilt pray
on our behalf. So then

7. Virgin, O Saint, O Bearer of God, since thou didst bring
forth the KING, a marvellous mystery dwelt upon thee for our
salvation. We will hold our peace, for we are unable to search
into the matter completely, as the greatness thereof rquireth,
and will describe that Doer of good things, through the
exceedingly great wonder of the manifestation. So then
8. He was the Living Word of the Father Who came down on
Mount SINAI, and gave the Law to MOSES (Exodus xix. 16
ff.) whilst the top of the mountain was covered with mist, and
with smoke, and with darkness, and with storm, and with the
terrifying blasts of trumpets. He admonished those who were
standing there in fear, So then

9. It was He Who came down to thee, O rational mountain, in
the humility of the Lover of men. Without any change He
became incarnate of thee, and took a perfect body, endowed
with reason and like unto ourselves, through the spirit of
wisdom. God took up His abode on her and became perfect
man so that He might deliver ADAM, and forgive him his sin,
and make him to dwell in heaven, and bring him back to his
former state in His abundant compassion and mercy. So then

10.It is impossible for any to describe the greatness of
the Virgin. For God chose her, and He came and dwelt upon
her. He Who dwelt in the light, Whom none could approach,
was carried in her womb nine months. He Who is invisible, He
Who is incomprehensible did MARY bring forth, being a
virgin. So then

11. This is the stone which DANIEL the prophet saw, which
was hewn from a high mountain, without hands (Daniel ii. 34,
35), that is to say, the Word Who went forth from the Father.
He came and became incarnate of the Virgin without seed of
men, and delivered us. So then

12. Thou art the pure twig and the right vessel of the True
Faith of the saints our Fathers. O thou pure God bearer, O thou
sealed Virgin, thou didst bring forth for us the Word of the
Father, JESUS CHRIST. He came and He hath delivered us. So then

13. Thou art the Mother of the Glorious Light, O God bearer.
Thou didst carry the Word Who is invisible, and after thou
hadst brought Him forth thou didst continue to be a virgin. With
praise and blessing shall men magnify thee. So then

14. What tongue is able to proclaim that which should be
declared concerning thee, O thou pure Virgin, Mother of the
Light, the Word of the Father? Thou wast the throne of the
KING Whom the Cherubim carry. We ascribe blessings unto
thee, O blessed woman, and we will remember thy name from
generation to generation, O Beautiful Dove, Mother of our Lord
JESUS CHRIST. So then

15. Rejoice thou, O MARY, Mother and Maid, for unto Him
Who is in thy bosom the angles bring praises, and the Cherubim
bow down and worship Him in fear, and the Seraphim spread
out their wings, and say concerning Him ceaselessly, “This is
the KING of Glory.” He came to forgive the sins of the world
in the greatness of His Compassion.

1. ኵሉ ሠራዊተ ሰማያት ይብሉ ብፅዕት አንቲ ሰማይ ዳግሚት ዲበ ምድር፡፡ ኆኅተ ምሥራቅ ማርያም ድንግል ከብካብ ንጹሕ ወመርዓ ቅዱስ፡፡ ነጸረ ኣብ እምሰማይ ወኢረከበ ዘከማኪ፡፡ ፈነወ ዋህዶ ወተሰብአ እምኔኪ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

2. ኲሉ ትውልድ ያስተበፅዑኪ ዕቢያተ ለኪ ለባሕቲትከ አ እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ፡፡ ተነበዩ ላዕሌኪ ዕቢያተ ወመንክራተ ሀገረ እግዚአብሔር እስመ ኮንኪ አንቲ ማኅደረ ለፍሡሐን፡፡ ኵሎሙ ነገሥተ ምድር የሐውሩ በብርሃንኪ ወአሕዛብኒ በጸዳልኪ ኦ ማርያም ኲሉ ትውልድ ያስተበፅዑኪ ወይሰግዱ ለዘተወልደ እምኔኪ ወየዐብይዎ። ሰኣሊ ለነ ቅድስት፡፡

3. አንቲ ዘበአማን ደመና እንተ አስተርአይኪ ለነ ማየ ዝናም፡፡ ትእምርተ ዋህዱ ረሰየኪ አብ መንፈስ ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ ወኀይለ ልዑል ጸለለኪ ኦ ማርያም አማን ወለድኪ ቃለ ወልደ አብ ዘይነብር ለዓለም መጽአ ወአድኅነነ እምኃጢአት፡፡ ዐቢይ ውእቱ ክብር ዘተውህበ ለከ ኦ ገብርኤል መልአክ ዜናዊ ፍሡሐ ገጽ ሰበከ ለነ ልደተ እግዚእ ዘመጽአ ኀቤነ ወአብሠርካ ለማርያም ድንግል ዘእንበለ ርስሐት ወትቤሳ ተፈሥሒ ኦ ምልእተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

4. ረከብኪ ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ ወኃይለ ልዑል ጸለለኪ ኦ ማርያም ኣማን ወለድኪ ቅዱሰ፡፡ መድኅኑ ለኵሉ ዓለም መጽአ አድኃነነ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

5. ግብረ ድንግል ይሴብሕ ልሳንነ ዮም ንወድሳ ለማርያም ወላዲተ አምላክ በእንተ ዘተወልደ እምኔሃ በሀገረ ዳዊት እግዚእነ ወመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ንዑ ኵልክሙ አሕዛብ ናስተብጽዓ ለማርያም እስመ ኮነት እመ ድንግላ ወጽሙረ፡፡ ተፈሥሒ ኦ ድንግል ንጽሕት እንተ አልባቲ ርኲስ ዘመጽአ ቃለ አብ ወተሰብአ እምኔሃ፡፡ ተፈሥሒ ኦ ሙዳይ እንተ አልባቲ ነውር ፍጽምት ዘአልባ ርስሐት፡፡ ተፈሥሒ ኦ ጎነት ነባቢት ማኅደሩ ስክርስቶስ ዘኮነ ዳግማይ አዳም በእንተ አዳም ቀዳሚ ብእሲ። ተፈሥሒ ኦ ጸዋሪቱ ለዋህድ ዘኢተፈልጠ አምኅፅነ አቡሁ። ተፈሥሒ ኦ ከብካብ ንጹሕ ሥርግው በኵሉ ሥነ ስብሐት መጽአ ወተሰብአ እምኔኪ ተፈሥሒ ኦ ዕፀ ጳጦስ እንተ ኢያውዐያ እሳተ መለኮት፡፡ ተፈሥሒ ኦ አመት ወእም ድንግል ወሰማይ ሰማያዌ እንተ ፆረት በሥጋ ዘይጼዐን ዲበ ኪሩቤል። ወበእንተዝ ንትፈሣሕ ወንዘምር ምስለ መላእክት ቅዱሳን፡፡ በፍሥሐ ወበሐሤት ወንበል ስብሐት ለእግዚኣብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ እስመ ኪያኪ ሠምረ ዘሎቱ ክብር ወስብሐት ሰአሊ ለነ ቅድስት።

6. የዐቢ ክብራ ለማርያም እምኵሎሙ ቅዱሳን እስመ ድልወ ኮነት ለተወክፎ ቃለ አብ ዘይፈርህዎ መላእክት ወየአኵትዎ ትጉሃን በሰማያት፡፡ ፆረቶ ማርያም ድንግል በከርሣ፡፡ ይእቲ ተዕቢ እምኪሩቤል ወትፈደፍድ እምሱራፌል እስመ ኮነት ታቦተ ለአሐዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ ዛቲ ይእቲ ኢየሩሳሌም ሀገሮሙ ለነቢያት ወማኅደረ ፍሥሓሆሙ ለኵሎሙ ቅዱሳን፣ ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ወጽላሎተ ሞት ብርሃን ዐቢይ ሠረቀ ላዕሌሆሙ እግዚአብሔር ዘየዕርፍ በቅዱሳኒሁ ተሰብአ እምድንግል ለመድኀኒት ዚኣነ ርእዩ ዘንተ መንክረ። ወዘምሮ ዘምሩ በእንተ ምሥጢር ዘተከሥተ ለነ እስመ ዘኢይሰባእ ተሰብአ ቃል ተደመረ፡፡ ወዘአልቦ ጥንት ኮነ ቅድመ ወለዘአልቦ መዋዕል ኮነ ሎቱ መዋዕል፡፡ ዘኢይትዐወቅ ተከሥተ ወዘኢይትረአይ ተርእየ፡፡ ወልደ እግዚብሔር ሕያው ጥዩቀ ኮነ ሰብአ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘትማልም ወዮም ወክመ ውእቱ እስከ ለዓለም፡፡ አሐዱ ህላዌ ሎቱ ንስግድ ወንሰብሕ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

7. ሕዝቅኤል ነቢይ ኮነ ስምዐ በእንቲኣሃ ወይሴ ርኢኩ ኆኅተ በምሥራቅ ኅቱም በዐቢይ መንክር ማኅተም አልቦ ዘቦአ ዘእንበለ እግዚኣ ኀያላን ሶኣ ውስቴታ ወወፅአ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

8. ኖኅትስ ድንግል ይእቲ እንተ ወለደት ለነ መድኅነ እምድኅረ ወለደት ኪያሁ ነበረት በድንግልና ከመ ትካት፡፡ ቡሩክ ውእቱ ፍሬ ከርሥኪ ኦ ወላዲተ እግዚእ ዘመጽኣ ወአድኅነነ እምእደ ጸላዒ ዘአልቦ ምሕረት:: አንቲ ፍጽምት ወቡርክት፡፡ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ ንጉሠ ስብሐት አምላክ ዘበአማኝ ለኪ ይደሉ ዕበይ ወክብር እምኵሎሙ እለ ይነብሩ ዲበ ምድር፡፡ ቃለ አብ መጽአ ወተሰብአ እምኔኪ፡፡ ወአንሶሰወ ምስለ ዕብእ፡፡ እስመ መሐሪ ውእቱ ወመፍቀሬ ሰብእ አድኅነ ነፍሳቲነ በምጽአቱ ቅዱስ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

1. የምድር ሁለተኛ የሆንሽ ሰማይ ሆይ የሰማያት ሠራዊት (መላእክት) ንዕድ ነሽ ይላሉ ድንግል ማርያም የምሥራቅ ደጅ ናት:: ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጹሕት የሠርግ ቤት ናት:: አብ በሰማይ አይቶ አንድ ልጁን ላከው በአንችም ሰው ሆነ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

2. ኣምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንችን ያመሰግኑሻል። የእግዚአብሔር ሀገር (ከተማ) ሆይ ነቢያት ድንቅ ድንቅ ነገርን ተናገሩልሽ ደስ የተሰኙ የጻድቃን ማደሪያ ሆነሻልና የምድር ነገሥታት ሁሉ በብርሃንሽ ይሄዳሉ። ሕዝቡም (ሠራዊቶቻቸውም) በብርሃንሽ ይሄዳሉ፣ ማርያም ሆይ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል። ካንቺ ለተወለደውም ይሰግዱለታል ያገኑታልም። ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

3. የዝናብ ውሃ የታየብሽ የእውነት ደመና አንቺ ነሽ፡፡ አብ የልጁ ምልክት አደረገሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይል ጋረደሽ ፣ ማርያም ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር የአብን ልጅ ቃልን የወለድሽልን መጥቶም ከኃጢአት አዳነኝ። ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምሥራችን የተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው ወደእኛ የመጣ የጌታን ልደት ነገርከን ለድንግል ማርያም ጸጋን የተመሳሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሠርካት፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

4. ጸጋን አገኘሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይልም ጋረደሽ (ጸለለብሽ) ማርያም ሆይ በእውነት ቅዱሱን ወለድሽ ዓለምን ሁሉ የሚያድን መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

5. አንደበታችን የድንግልን ሥራ ያመሰግናል፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት አገር ከእርስዋ ስለተወለደ አምላክን የወለደች ማርያምን ዛሬ እናመስግናት አሕዛብ ኑ ማርያምን እናመስግናት። እናትና ድንግል ሁለቱንም ሆናለችና። ርኩሰት የሌስብሽና የአብ ቃል መጥቶ ካንቺ ሰው የሆነ ንጽሕት ድንግል ሆይ ደስ ይሰልሽ ነውር የሌለብሽ ፍጽምትና ጉድፍ የሌለብሽ ሙዳይ ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ስለቀደመ ሰው አዳም ሁለተኛ አዳም የሆነ የክርስቶስ ማደሪያው የምትናገሪው ገነት ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ከአባቱ ያልተለየ አንድ የተሸከምሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ በክቡር ጌጥ ሁሉ ያጌጠ እርሱ መጥቶ ሰው የሆነብሽ ንጽሕት የሠርግ ቤት ሆይ ደስ ይበልሽ የመለኮት እሳት (ባሕርይ) ያላቃጠለሽ ጳጦስ ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ በኪሩቤል የሚቀመጠውን ሰማያዊ ሥጋን የተሸከምሽ ገረድና እናት ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ነለዚህ ንጹሐን ከሆኑ መላእክት ጋር በፍጹም ደስታ ተሰኝተን እናመስግን በሰማይም ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ዕርቅ ይሁን እንበል ክብርና ምስጋና ጌትነት ያለው እርሱ አንችን ወድዋልና ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

6. ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፣ የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና። መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማያት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማኀፀንዋ ተሸከመችው። ይህች ከኪሩቤል ትበልጣለች፣ ከሱራፌልም ትበልጣለች ከሦስቱ አካል ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና፡፡ የነቢያት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም ይህች ናት። ለቅዱሳን ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው። በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳኝ ልዩ ከሆነች ከድንግል ሰው ሆኗልና፡፡ ኑ ይህን ድንቅ እዩ፡፡ ሰስ ተገለጠልን ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ። ሰው የማይሆን ሰው ሆኖዋልና፣ ቃል ተዋህዷልና። ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት። የማይታወቅ ተገለጠ የማይታይ ታየ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በርግጥ ሰው ሆነ። ትላንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለትና እናመሰግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

7. ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለ እርስዋ መሰከረ ድንቅ በሆነ ታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ ምሥራቅ አየሁ አለ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርስዋ ገብቶ የወጣ የለም ቅድስት ሆይ ለምኝልን::

8. ኖኀትም ደጅም መድኃኒታችንን የወለደች ድንግል እርሱን ከወለደች በኋላ እንደ ቀድሞ በድንግልና ኖራለችና። መጥቶ ምሕረት ከሌለው ጠላት እጅ ያዳነን ጌታን የወለድሽ ሆይ የማኅፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው፣ አንቺ ፍጽምትና የተባረክሽ ነሽ የእውነት አምላክ በሆነ ባክብር ባለቤት ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና በምድር ላይ ከሚኖር ሁሉ ይልቅ ገናንነትና ክብር ለአንቺ ይገባል። የአብ ቃል መጥቶ በአንቺ ሰው ሆነ፡፡ ከሰው ጋርም ተመሳስሰ። መሐሪ ይቅር ባይ ሰውን ወደጅ ነውና በልዩ አመጣጡ አዳነን፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

1. All the hosts of the heavens say, “Blessed art thou, O thou
second heaven upon the earth, Door of the sunrise (or, the
East), MARY the Virgin, thou pure Bride-chamber of the Holy
Bridegroom. The Father looked down from heaven, and found
none like unto thee; He sent His only One, and He became
incarnate of thee. All generations shall ascribe blessings unto
thee, thou who alone art our Lady, the Bearer of God.”

2. Great and wonderful things have [the Prophets] prophesied
concerning thee, O City of God, for thou art the abode of all
those who rejoice. All the kings of the earth walk in thy light
and [all] the nations in thy splendour (Isaiah lx. 3). O MARY,
all generations shall ascribe blessings unto thee, and shall
worship Him Who was brought forth by thee, and shall magnify
Him. All [of them].

3. Thou art in very truth the Cloud, and thou hast shown us the
water of the rain, the sign of the Onlybegotten. The Father
established thee, the Holy Ghost took up His abode on thee,
and the power of the Most High overshadowed thee, O MARY,
and verily thou didst bring forth the Word, the Son of God,
Who endureth for ever. He came and hath delivered us from
sin. Great was the honour that was bestowed upon thee, O
GABRIEL, the Angel of the Annunciation with the joyful face.
Thou didst proclaim unto us the birth of the Lord, Who hath
come to us, and thou didst announce Him to MARY, the
spotless Virgin, and didst say unto her, “Rejoice thou, O thou
who art full of grace, God is with thee” (Luke i. 28). All [of
them].

4. Thou didst find grace, the Holy Spirit dwelt upon thee, and
the power of the Most High overshadowed thee, O MARY.
Verily thou didst bring forth the Holy Saviour for all the world.
He came and He hath delivered us. All [of them].

5. Our tongue this day praiseth the work of the Virgin. We
praise MARY, the God-bearer, because our Lord and Redeemer
JESUS CHRIST was born of her in the city of DAVID. Come,
O all ye nations, and let us ascribe blessing unto MARY, for
she is at once mother and virgin. Rejoice, O pure Virgin, in
whom there is no blemish, to whom came the Word of the
Father, Who was incarnate of her. Rejoice, O Vessel
unblemished, perfect, and spotless Woman. Rejoice thou, O
Garden endowed with reason, thou Abode of CHRIST, Who
became the Second ADAM because of the First ADAM, the
man. Rejoice thou, O woman who borest the Onlybegotten,
Who, having gone forth from the bosom of His Father, suffered
no change. Rejoice, O thou pure Bride-chamber, who art
adorned with all the beauty of praise, He came and was not
consumed by the fire of the Godhead. Rejoice thou, O Mother
and Maid, Virgin, thou second heaven, who didst carry in thy
body Him Who is borne aloft by the Cherubim and Seraphim.
And because of this we rejoice, and we sing with the holy
angels with joy and gladness, and we say, “Glory to God in the
heavens, and peace upon earth, His good will to men” (Luke ii.
14). For He unto Whom belong glory and praise for ever and
ever is well-pleased with thee. Amen. All [of them].

6. The glory of MARY is greater than that of all the saints, for
she was worthy to receive the Word of the Father. Him Who
maketh the angels to be afraid, Him Whom the Watching
Angels in heaven praise, did MARYthe Virgin carry in her
womb. She is greater than the Cherubim, and superior to the
Seraphim, for she was the Ark (or, Tabernacle) of One of the
Holy Trinity. She is JERUSALEM, the city of the Prophets,
and she is the habitation of the joy of all the saints. On the
people who sat in darkness and the shadow of death hath a great
Light risen. God Who resteth in His holiness became incarnate
of a virgin for our salvation. Come ye and look upon this
marvellous thing, and sing ye His song because of the mystery
that hath been revealed unto us. For He Who was became a
man, the Word mingled [with our nature], He Who had no
beginning [assumed] a beginning for Himself, and He Who had
no days [reckoned] to Himself days, and He Who could not be
known became revealed, and He Who was invisible showed
Himself; the Son of the Living God became a man indeed,
JESUS CHRIST, yesterday, to-day, and for ever (Hebrews
xiii.8), One Nature, Him do we worship and praise. All [of
them].

7. EZEKIEL the Prophet testified concerning her and said, “I
see a sealed door in the East, sealed with a great and wonderful
seal, and no one save the God of the mighty ones hath gone in
through it. He went in and He came out” (Ezekiel xliii. 4; xliv,
1, 2). All [of them].

8. This door is the Virgin who brought forth for us the
Redeemer. She brought Him forth, and she remained in her
virginity after she had brought Him forth. Blessed is the Fruit of
thy womb, O Godbearer, Who came and delivered us out of the
hand of the Enemy who was merciless, Complete art thou and
blessed; thou hast found grace with the KING of Glory, the
God in truth. Majesty and glory belong to thee more than to all
those who dwell upon the earth. The Word of the Father came
and was incarnate of thee, and walked about with men, for He
is compassionate and a Lover of men. He delivered our souls by
His holy coming.

1. ዕፀ እንተ ርእየ ሙሴ በነደ እሳት ዉስተ ገዳም ወአዕፁቂሃ ኢትዉዒ፡ ትመስል ማርያም ድንግል ዘእንበለ ርኩስ ተሰብአ እምኔሃ ቃለ አብ፡ ወኢያዉዐያ እሳተ መለኮቱ ለድንግል፡ እምድኅረ ወለደቶ ድንግልናሃ ተረክበ፡ ወመለኮቱ ኢተወለጠ ኮነ ወልደ ዕጓለ እመሕያዉ አምላክ ዘበአማን መጽአ ወአድኃነነ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

2. ናዓብየኪ ኩልነ ኦ እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ ይኩን ላእለ ኩልነ፡፡

3. ትምክህተ ኩልነ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ዘበእንቲአሃ ተስእረ ዘቀዳሚ መርገም እንተ ኀደረት ዲበ ዘመድነ በእልወት ዘገብረት ብእሲት በልአት እምዕፅ በእንተ ሔዋን ተአፅወ ኆኅተ ገነት ወበእንተ ማርያም ድንግል ተርኅወ ለነ ዳግመ ከፈ ለነ ንብላዕ እምፀ ህይወት ዘውእቱ ስጋሁ ለክርስቶስ ወደሙ ክቡር በእንተ ፍቅረ ዚአነ መፅአ ወአድኀነነ አይ ልቡና ወአይ ነቢብ ወአይ ሰሚዕ ዘይክል አእምሮ ዝንቱ ምስጢር መንክራተ ዘይትነበብ ላእሌሃ እግዚአብሔር መፍቀሬ ሰብእ ፩ዱ ውእቱ ባህቲቱ ቃለ አብ ዘሀሎ እምድመ አለም በመለኮቱ እንበለ ሙስና እም፩ዱ አብ መጽአ ወተሰብአ ወልድ ዋህድ እምቅድስት እሙ እምድኅረ ወለደቶ ኢማሰነ ድንግልናሃ ወበእንተዝ ግህደ ኮነት ከመ ወላዲተ አምላክ ይእቲ ኦ እሙቅ ብዕለ ፀጋ ጥበቡ ለእግዚአብሔር ከርሥ ዘፈትሐ ላእሌሃ ትለድ በፃዕር ወሕማም ወሐዘነ ልብ ወኮነት ፈልፈለ ህይወት ወወለደት ዘእንበለ ዘርአ ብእሲ ዘይስዕር መርገመ እምዘመድነ እንዘ ንብል ስብሐት ለከ ኦ መፍቀሬ ሰብእ ኄር ወመድሃኔ ነፍሳቲነ ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

 

 

4. ኦዝ መንክር ወእፁብ ኀይለ ከርሳ ለድንግል ወላዲተ አምላክ ዘእንበለ ዘርዕ ስምአ ኮነ መልአክ ዘአስተርአዮ ለዮሴፍ እንዘ ይብል ከመዝ እስመ ዘይትወለድ እምኔሃ እመንፈስ ቅዱስ ቃለ አብ እግዚአብሔር ውእቱ ተሰብአ ዘእንበለ ውላጤ ወለደቶ ማርያም ምክቢተ ዝንቱ ፍስሐ ወይቤ ትወልዲ ወልደ ወይሰመይ አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ ወዓዲ ይሰመይ ኢየሱስሃ ዘያድህኖሙ ለህዝቡ እምኃጢአቶሙ ያድኅነነ በኀይሉ ወይስረይ ኃጢአተነ እስመ ጥዩቀ አእመርናሁ ከመ አምላክ ውእቱ ዘኮነ ሰብአ ሎቱ ስብሐት እስከ ለዓለም፡፡

 

ኦዝ መንክር ልደተ አምላክ እማርያም እምቅድስተሸ ድንግል አግመረቶ ለቃል ኢቀደሞ ዘርዕ ለልደቱ ወኢአማሰነ በልደቱ ድንግልናሃ እኀበ አብ ወጽአ ቃል ዘእንበለ ድካም ወእምድንግል ተወልደ ዘእንበለ ህማም ሎቱ ሰገዱ ሰብአሰገል አምፅዑ እጣነ ከመ አምላክ ውእቱ ወርቀ እስመ ንጉስ ውእቱ ወከርቤ ዘይትወሃብ ለሞቱ ማህየዊ በእንቲአነ ተወክፈ በፈቃዱ ፩ዱ ውእቱ ባህቲቱ ኄር ወመፍቀሬ ሰብእ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

5. ኦዝ መንክር ነሥአ አሐደ ዐፅመ እምገቦሁ ለአዳም ወለሐኰ እምኔሁ ብእሲተ ወኩሎ ፍጥረተ ዕጓለ እመሕያዉ፡ ተዉህበ እግዚእ ቃለ አብ ተሰብአ እምቅድስት ድንግል ወተሰምየ ኣማኑኤል ወበእንተዝ ንስአል ኀቤሃ ኩሎ ጊዜ ከመ ታስተሥሪ በእንቲአነ ኀበ ፍቁር ወልዳ፡ ኄርት ይእቲ በኀበ ኩሎሙ ቅዱሳን ወሊቃነ ጳጳሳት እስመ ኣምጽአት ሎሙ ዘኪያሁ ይጸንሑ፡ ወለነብያትኒ ኣምጽአት ሎሙ ለዘበእንቲኣሁ ተነበዩ፡ ወለሐዋርያትኒ ወለደት ሎሙ ዘሰበኩ በስሙ ዉስተ ኩሉ ኣጽናፈ ዓለም፡ ለሰማዕት ወለመሃይምናን ወፅአ እምኔሃ ዘተጋደሉ በእንቲአሁ ክርስቶስ ብዕለ ጸጋ ጥበቡ ዘኢይትዐወቅ፡ንኅሥሥ ዕበየ ሣህሉ መጽአ ወአድኃነነ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

 

6. መሐለ እግዚአብሔር ለዳዊት በፅድቅ ወኢይኔስሕ እስመ እምፍሬ ከርስከ አነብር ዲበ መንበርከ፡፡ ወሶበ ተወክፎ ውእቱ ፃድቅ ከመ እምኔሁ ይትወለድ ክርስቶስ በስጋ ፈቀደ ይኅሥሥ ወይርከብ ማኅደሮ ዘእግዚአብሔር ቃል፡፡ ወፈፀመ ዘንተ በአብይ ትጋህ ወእምዝጸርሐ በመንፈስ ወይቤ ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ ወማህደሮ ለአምላከ ያዕቆብ

እንተ ይእቲ ቤተልሔም ዘሐረያ አማኑኤል ይትወለድ ውስቴታ በሥጋ ለመድሃኒተ ዚአነ ካዕበ ይቤላ ካልእ እምነቢያት አንቲኒ ቤተልሔም ምድረ ኤፍራታ ኢትቴሐቲ እምነገሥተ ይሁዳ ፡፡ እስመ እምኔኪ ይወፅእ ንጉስ ዘይርእዮሙ ለሕዝብየ እስራኤል ኦዝ ነገር ለእሉ እለ ተነበዩ ዘበአሐዱ መንፈስ በእን ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት ምስለ ኄር አቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ እምይእዜ ወእስከ ለዓለም ፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

7. ዳዊት ዘነግሠ ለእስራኤል አመ ይትነሥኡ ላዕሌሁ ዕልዋን ፈተወ ይስተይ ማየ እምአዘቅተ ቤተልሔም ፍጡነ ተንሥኡ መላህቅተ ሐራሁ ወተቃተሉ በውስተ ትእይንተ ዕልዋን ወአምጽኡ ሎቱ ውእተ ማየ ዘፈተወ ይስተይ ፡፡ ወሶበ ርእየ ውእቱ ጻድቅ ከመ አጥብዑ ወመጠዉ ነፍሶሙ ለቀትል በእንቲአሁ ከዐወ ውእተ ማየ ወኢሰትየ እምኔሁ ወእምዝ ተኈለቆ ሎቱ ጽድቅ እስከ ለዓለም ፡፡ አማን መነኑ ሰማእት ጣእማ ለዛ አለም ወከዐዉ ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተዐገሱ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት፡፡ ተሣሀለነ በከመ ዕበየ ሣህልከ ፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡


8. አሐዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ ርእዮ ትሕትናነ አጽነነ ሰማየ ሰማያት፡፡ መጽአ ወኀደረ ውስተ ከርሠ ድንግል ወኮነ ሰብአ ከማነ ዘእንበለ ኀጢአት ባሕቲታ፡፡ ወተወልደ በቤተልሔም በከመ ሰበኩ ነቢያት፡፡ አድኀነነ ወቤዘወነ ወረሰየነ ሕዝበ ዚአሁ ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት

፩፤ ርኵሰት የሌለባት ድንግል ማርያም ሙሴ በበረሃ በነደ እሳት ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ያያት ዕፅን ትመስላለች፤ የአብ ቃል በርስዋ ሰው ሆኗልና፣ እሳተ መለኮቱ (የመለኮቱ ባሕርይ) አላቃጠላትምና ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ አልተለወጠምና ሰውም ቢሆን መለኮቱ አልተለወጠም በዕውነት አምላክ ነውና በዕውነት አምላክ የሆነ እርሱ መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፪፤ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ሁላችን እናገንሻልን። ይቅርታሽ ለሁላችን ይሆን ዘንድ ነውና።

፫፤ ሔዋን እንጨት በልታ ባደረገችው ዓመፅ በባሕርያችን ያደረ የቀድሞው እርግማን በእርስዋ የጠፋልን አምላክን የወለደች ድንግል ማርያም የሁላችን መመኪያ ናት። ስለ ሔዋን የገነት ደጅ ተዘጋ ዳግመኛም ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን። ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ አደለን። ይኸውም እኛን ስለመውደድ መጥቶ ያዳነን የክርስቶስ ክብር ሥጋው ክብር ደሙ ነው። ስለ እርሷ ድንቅ ሆኖ የሚነገረውን ይህን ምሥጢር ማወቅ የሚቻለው ምን ልቡና ነው? መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? መስማት የሚቻለው ምን ጆሮ ነው? ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር አንድ ብቻ የሆነ አምላክነቱ ሳይለወጥ ከዓለም በፊት የነበረ የአብ ቃል ከአብ ዘንድ መጥቶ ልዩ ከሆነች እናቱ ሰው ሆነ። ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ አልተለወጠም። ስለዚህ አምላክን የወለደች እንደሆነች ታወቀች። የእግዚአብሔር የጥበቡ ስፋት ምን ይጠልቅ? በጻእር በምጥ በልብ ጋር ትወልድ ዘንድ የፈረደባት ማኅፀን የሕይወት መገኛ ሆነች ከባሕርያችን እርግማንን የሚያጠፋልንን ያለ ወንድ ዘር ወለደችልን። ስለዚህም ሰውን የምትወድ ሆይ ክብር ላንተ ይገባል፤ ቸርና የሰውነታችን መድኃኒትም ነህ እያልን እናመስግነው። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፬፤ ያለ ወንድ ዘር አምላክን የወለደች ድንግል የማኅፀንዋ ሥራ ምን ይደንቅ? ለዮሴፍ የታየው መልአኩ ከእርሷ በመንፈስ ቅዱስ የሚወለደው ያለ መለወጥ ሰው የሚሆነው የእግዚአብሔር ቃል ነው ብሎ መስክሯልና። ማርያም የዚህ ደስታ ዕፅፍ የሆነ እርሱን ወለደችው። መልአኩ ልጅ ትወልጃለሽ ስሙም አማኑኤል ይባላል አላት። ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው። ዳግመኛ ወገኖቹን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ኢየሱስ ይባላል። በችሎታው (በኃይሉ) ያድነን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘለዓለም ክብር ይግባውና ሰው የሆነ እርሱን አምላክ እንደሆነ በተረዳ ነገር አውቀነዋልና። ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ ቃልን ወሰነችው። ልደቱንም ዘር አልቀደመውም። በመወልዱም ንግልናዋን አልለወጠውም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ። ከድንግልም ያለ ሕማም ተወለደ። ሰብአ ስገል ሰገዱለትም አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት ንጉሰም ነውና ወርቅ አመጡለት ስለእኛ በፈቃዱ ለተቀበለው መዳኛችን ለሆነ ሞቱም ከርቤ አመጡለት። ቸር ሰውን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው ። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፭፤ ከአዳም ጎን አንዲት ዐፅም ማንሣት ምን ይደንቅ? ከእርሱ ሴትን ፈጠረ የሰው ፍጥረትንም ሁሉ ፈጠረ። ጌታ የአብ ቃል ተሰጠ። ከልዩ ድንግልም ሰው ሆነና አማኑኤል ተባለ ስለዚህ ሁል ጊዜ እርስዋን እንለምን፣ ከተወደደ ልጅዋ ታማልደን ዘንድ። በቅዱሳንና በሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ቸር ናት ደጅ የሚጠኑትን ወልዳላቸዋልችና ለነቢትም ትንቢት የተናገሩለትን ወልዳላቸዋለችና ለሐዋርያትም እስከ ዓለም ዳርቻ በስሙ ያስተማሩለትን ወልዳላቸዋለችና ሰማዕታትና ምዕመናንም የተጋደሉለትን የጥበቡ ጸጋ ብዛት የማይታወቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርስዋ ተወልዷልና የይቅርታውን ብዛት መርምረን እንወቅ (እንገፈልግ) መጥቶ አድኖናልና። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፮፤ እግዚአብሔር የባሕርይህን ፍሬ በዙፋንህ አኖራለው ብሎ ለዳዊት በእውነት ማለ እይጸጸትም። ጻድቅ እርሱ ዳዊት ክርስቶስ በሥጋ ከእርሱ እንዲወለድ ባመነ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ማደሪያ ፈልጎ ያገኝ ዘንድ ወደደ ይህንንም በታላቅ ትጋት ፈጸመ። ከዚህም በኋላ እነሆ በኤፍራታ ሰማነው ብሎ በመንፈስ ቅዱስ አሰምቶ ተናገረ። ይህቺውም አማኑኤል እኛን ለማዳን በሥጋ ይወልድባት ዘንድ የመረጣት የያዕቆብ አምላክ ማደሪያ ናት። ዳግመኛም ከነቢያት አንዱ ሚክያስ አንቺ የኤፍራታ ክፍል የሆንሽ ቤተልሔም ከይሁዳ ነገሥታት መሳፍንት አገር አታንሺም ወገኖቼ እሥራኤልን የሚጠብቃቸው ንጉሥ ካንቺ ይወጣልና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከቸር አባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ምስጋና ስለተገባው ስለ ክርስቶስ ባንድ መንፈስ ቅዱስ ትንቢት የተናገሩት የነዚህ የሚክያስና የዳዊት ነገር ምን ይረቅ? ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፯፤ ለእስራኤል የነገሠ ዳዊት ጠላቶቹ በተነሡበት ጊዜ ከቤተልሔም ምንጭ ውኃ ይጠጣ ዘንድ ወደደ የጭፍሮቹ አለቆች ፈጥነው ተነሡና በጠላቶቹ ከተማ ተዋግተው ሊጠጣ የወደደውን አመጡለት። ጻድቅ ዳዊት ግን ጨክነው ሰውነታቸውን ስለ እርሱ ለጦርነት ለሞት አሳልፈው እንደ ሰጡ ባየ ጊዜ ያን ውኃ አፈሰሰ ከእርሱም አልጠጣም ከዚህ በኋላ ለዘለዓለም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በዕውነት ናቁ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ። ስለ መንግሥተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ። እንደ ይቅርታህ ብዛት ይቅር በለን። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፰፤ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ መዋረዳችንን አይቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ባሕርዩን ዝቅ አደረገና መጥቶ በድንግል ማኅፀን አደረ። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀርም አንደኛ ሰው ሆነ፤ ነቢያት ትንቢት እንደተናገሩለት በቤተልሔም ተወለደ። ፈጽሞ አዳነን ወገኖቹም አደረገን። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

1. The Bush which MOSES saw in flaming fire in the desert the wood of which was not consumed is a similitude of MARY, the Virgin who was spotless. The Word of the Father became incarnate of her, and the fire of His Godhead did not consume the Virgin, and after she had brought Him forth her virginity was maintained, and His Godhead was unchanged. Our God, Who verily is God, became a man; He came and delivered us. We all magnify thee, O our Lady, the Godbearer, that thy compassion may be over us all. 

2. The VIRGIN MARY, the God-bearer, hath become the object of the boast of all of us, because through her was destroyed the curse of olden time, which rested upon our race, through the wickedness which the woman committed [when] she ate [of] the tree. Through EVE was the door of the Garden shut fast, and because of MARY the Virgin it hath been opened to us again. It is allotted to us to eat of the Tree of Life, that is to say, the Body of CHRIST and His precious Blood. Because of His love for us He came and delivered us. What understanding, and What language, and What hearing is able to comprehend this mystery, which must be proclaimed to be wonderful, “God is the lover of men?” One is He Alone, the Word of the Father, Who existed before the world in His incorruptible Godhead, from One, the Father. The Onlybegotten Son came and was incarnate of the holy woman His mother, and after she brought Him forth her virginity perished not, and because of this it became manifest that she was the Bearer of God. O deep is the richness of the wisdom of God! The womb which He decreed should bring forth children in pain, and suffering, and sorrow of heart, hath become the fountain of life, and hath brought forth without the seed of man Him Who removed the curse from our race. And for this reason we will praise Him, saying, “Glory be unto Thee, O Thou Good Friend of man, the Redeemer of our souls.” We will magnify thee [,O MARY].  

3. O how wonderful and mighty in power was the womb of the Virgin, which brought forth God without seed! And of this the angel who appeared unto JOSEPH was a witness when he spake, saying, “That which shall be born of her is of the Holy Spirit” (Matthew i. 20). It was the Word of God Who became incarnate without change. MARY brought Him forth a second time. And GABRIEL rejoiced and said unto her, “Thou shalt bring forth a Son and shalt call His Name EMMANUEL, which is, being interpreted, God with us. And moreover, He shall be called JESUS, Who shall save His people from their sins” (Matthew i. 20, 24). And may He save us also be His power, and forgive our sins, because we have known in truth that He is the God Who became man. Praise be unto Him for ever and ever. O how wonderful is the birth of God by MARY, the Holy Virgin! She completed the Word of the Father; seed did not precede His Birth, and her virginity was not destroyed by His Birth. The Word went forth from the Father without weariness and was born of the Virgin without suffering (or, pain). The wise men worshipped Him, and brought unto Him incense because He was God, and gold because He was the KING, and myrrh, which was given for His death which gave life [unto men]. And for our sakes He accepted [death] of His own free will. He alone is the Good Being and the Lover of men. We will magnify thee [, O MARY].  

4. O how wonderful! He took a rib from the side of ADAM, and fashioned from it a woman, and the whole creation of the children of men was given to God, the Word of the Father, Who was incarnate of the Holy Virgin, and is called EMMANUEL. And because of this we beseech her at all times to strive on our behalf with her beloved Son for the forgiveness of our sins. She was beneficent towards all the saints and the high priests, for she brought to them that for which they waited, and she brought to the Prophets Him concerning Whom they had prophesied, and she brought forth to the Apostles Him in Whose Name they were to preach in all the ends of the world, and from her went forth for the martyrs and believers Him for Whom they were to fight, JESUS CHRIST. The richness of the grace of His wisdom cannot be fathomed. We will seek after the greatness of His compassion, for He came and delivered us. We will magnify thee [, O MARY]. 

5. God swore unto DAVID in righteousness, and He will not repent, “Of the fruit of thy belly I will seat upon thy throne” (2 Samuel vii., 12; Psalm cxxxii. 11). And when that righteous man received it from Him, that CHRIST should be born of him in the flesh, he wished to seek out and to prepare a dwelling-place for God, the Word of the Father. And he completed it with great effort and then he cried out in the Holy Sprit and said, “Behold, we have heard it in EFRÂTÂ and the dwelling-place of the God of JACOB, which is BETHLEHEM, in which EMMANUEL hath chosen to be born in the flesh for our salvation” (compare Psalm cxxxii. 6). 

6. And also another of the prophets hath said it: “And as for thee, O BETHLEHEM [of] the land of EFRÂTÂ, thou shalt not be the least of the kings of JUDAH, for from thee shall go forth a King Who shall rule My people ISRAEL” (Micah v.2). O how wonderful is the word of those who prophesied concerning CHRIST in one Spirit, to Whom be glory, together with His Good Father and the Holy Spirit, henceforth and for ever. We will magnify thee [, O MARY].

7. When evil men revolted against DAVID who reigned over ISRAEL, he wished to drink water from the pool of BETHELEHEM, whereupon straightway the captains of his hosts rose up, and waged war in the camp of the rebels, and brought unto him that water which he wished to drink. And when that righteous man saw that they had willingly delivered themselves over to slaughter for this sake, he poured out that water [unto the Lord] and did not drink of it (2 Samuel xxiii. 13-17; 1Chronicles xi. 18, 19). And then righteousness was accounted unto him for ever. And verily in like manner have the martyrs rejected the desire of this world, and poured out their blood for God, and have endured bitter death[s] for the sake of the kingdom of heaven. Have compassion upon us according to the greatness of Thy compassion. We will magnify thee [, O MARY].  

8. One of the Holy Trinity saw our low estate, bowed the heaven of heavens, came and dwelt in the womb of the Virgin, and became a man like unto us, with the exception of sin alone. And He was born in BETHLEHEM, according to what the Prophets preached, He delivered us, and redeemed us, and made us His own people for ever and ever

1. ቡርክት አንቲ እምአንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ ኦ ማርያም ወላዲተ አምላክ ዘእንበለ ርኩስ ሰረቀ ለነ እምኔኪ ፀሐየ ፅድቅ ወአቅረበነ ታሕተ ክነፊሁ እስመ ውእቱ ፈጠረነ ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት ፡፡

2. ለኪ ለባሕቲትኪ ኦ እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ እመ ብርሃን አንቲ ናዐብየኪ በስብሐት ወበውዳሴ፡፡

3. ቡርክት አንቲ ተአብዪ አምሰማይ ወትከብሪ እምድር ወላእለ ኩሉ ህሊናት መኑ ዘይክል ነቢበ እበየኪ ወአልቦ ዘይመስል ኪያኪ ኦ ማርያም መላእክት ያዐብዩኪ ወሱራፌል ይሴብሑኪ እስመ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል ወሱራፌል መፅአ ወኀደረ ውስተ ከርሥኪ መፍቀሬ ሰብዕ አቅረበነ ሐቤሁ ዘዚአነ ሞተ ነሥአ ወእንቲአሁ ህይወተ ወሀበነ ዘሌቱ ክብር ወስብሐት ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት ፡፡

4. ቡርክት አንቲ ማርያም ወቡርክት ፍሬ ከርሥኪ ኦ ድንግል ወላዲተ አምላክ ምክሖን ለደናግል ዘእምቅድመ ዓለም ህልው ወፅአ እምከርሥኪ ሥጋነ ነሥአ ወመንፈሶ ቅዱሰ ወሃበነ ወረሰየነ ዕሩያነ ምስሌሁ በብዝኀ ኂሩት ፡፡ አንቲ ተአብዪ እምብዙሐት አንስት እለ ነስአ ፀጋ ወክብረ ኦ ማርያም ወላዲተ አምላክ ሀገር መንፈሳዊት ዘኀደረ ላዕሌሃ እግዚአብሔር ልዑል እስመ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል ወሱራፌል በእራኅኪ ሐቀፍኪዮ ወዘይሴሲ ለኩሉ ዘሥጋበብዝኀ ኂሩቱ አኀዘ አጥባተኪ ወጠበወ ሐሊበ ዘውእቱ አምላክነ መድሃኔ ኩሉ ይርእየነ እስ ለዓለም ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ እስመ ውእቱ ፈጠረነ ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

5. ማርያም ድንግል ሙዳየ እፍረት ነቅዓ ፈልፈለ ማየ ህይወት ፍሬ ከርሳ አድኃነ ኲሎ ዓለመ ወሠአረ እምኔነ መርገመ ወገብረ ሰላመ ማእከሌነ በመስቀሉ ወበትንሳኤሁ ቅድስት አግብኦ ለብእሲ ዳግመ ውስተ ገነት ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት ፡፡

6. ማርያም ንፅሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማእምንት ሰአሊተ ምህረት ለውሉደ ሰብእ ሰአሊ ለነ ኀበ ክርስቶስ ወልድኪ ይስረይ ሐጢአተነ ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት ፡፡

7. ማርያም ድንግል ትፀርህ በቤተመቅደስ ወትብል የዓምር እግዚአብሔር ከመ አልብየ ዘየአምር ባዕድ / ዘአአምር ባዕደ ወኢምንትኒ ዘእንበለ ድምፀ ቃሉ ለመላእክ ዘአብሠረኒ በክብር ወይቤለኒ ሰላም ለኪ ኦ ቅድስት ድንግል ፆርኪ ዘይፀወር አግመርኪ ዘይትገመር ወአልቦ ዘያገምሮ ምንትኒ ይበዝኅ ውዳሴኪ ኦ ምልዕተ ፀጋ በኩሉ ክብር እስመ ኮንኪ አንቲ ማህደረ ቃለ አብ አንቲ ውእቱ መንጦላእት ስፍህት እንተ ታስተጋብኦሙ ለመሃይምናን ሕዝበ ክርስትያን ወትሜህሮሙ ሰጊደ ለሥሉስ ማህየዊ አንቲ ውእቱ ዘፆርኪ ዓምደ እሳት ዘርእየ ሙሴ ዘውእቱ ወልደ እግዚአብሔር መጽአ ወኃደረ ውስተ ከርሥኪ ኮንኪ ታቦቶ ፈጣሬ ሰማያት ወምድር ፆርኪዮ በከርስኪ ፱ተ አውራኃ አንቲ ማእምንት ለዘኢያገምርዎ ሰማያት ወምድር ኮንኪ ተንከተመ ለዕርገት ውስተ ሰማይ የዓቢ እምብርሃነ ፀሐይ አንቲ ውእቱ ምስራቅ ዘወፅአ እምኔኪ ኮከብ ብሩህ ዘነፀርዎ ቅዱሳን በፍስሐ ወበሐሴት ዘፈትሐ ላዕለ ሔዋን ትለድ በፃዕር ወሕማም አንቲሰ ማርያም ሰማዕኪ ዘይብል ተፈሥሒ ኦ ምልዕተ ፀጋ ወለድኪ ለነ ንጉሠ እግዚአ ኩሉ ፍጥረት መጽአ ወአድኀነነ እስመ መሐሪ ውእቱ ወመፍቀሬ ሰብእ በእንተዝ ንዌድሰኪ በከመ ገብርኤል መላእክ እንዘ ንብል ቡርክት አንቲ ማርያም ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ ተፈሥሒ ኦ ምልእተ ፀጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት ፡፡

 

፩፤ ከሴቶሽ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ። የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረክ ነው ያለርኵሰት አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ እውነተኛ ፀሐይ ከአንቺ ወጣልን (ጌታ ተወለደልን) በክንፈ ረድኤቱም አቀረበን። እርሱ ፈጥሮናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፪፤ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ የብርሃን እናት ነሽና አንችን ብቻሽን በክብር በምስጋና እናገንሻለን።

፫፤ የተባረክሽ አንቺ ከመላእክት ትበልጫለሽ ከደቂቀ አዳምም ትበልጫልሽ ከድቂቀ አዳምም ትበልጫለሽ። ከአሳቦች ሁሉ ትበልጫልሽ ገናንነትሽን መናገር የሚቻለው ማነው አንቺን የሚመስል የለምና። ማርያም ሆይ መላእክት ያገኑሻል ሱራፌልም ያመሰግኑሻል። በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ አድሮ የሚኖር ጌታ መጥቶ በማኅፀንሽ አድሮአልና። ሰውን የሚወድ ወደ እርሱ አቀረበን፣ ክብር ምስጋና ያለው እርሱ የእኛን ሞት ተቀብሎ የእርሱን ሕይወት ለእኛ ሰጠን።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፬፤ የደናግል መመኪያቸው አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ከዓለም በፊት የነበረ እርሱ ሰው ሆኖዋልና ከአንቺ ተወልደ ሥጋችንን ነሣ (ተዋሐደ) መንፈስ ቅዱስንም ሰጠን። በቸርነቱ ብዛት መሳዮቹ አደረገን ጸጋንና ክብርን ከተቀበሉ ብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫልሽ አምላክን የወለድሽ ማርያም ሆይ ልዑል እግዚአብሔር ያደረብሽ (የከተመበሽ) ረቂቅ ከተማ ነሽ። በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ የሚኖረውን ጌታን በመኻል እጅሽ ይዘሸዋልና። በቸርነቱ ብዛት ሥጋዊ ፍጥረትን ሁሉ የሚመግብ እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ። ይኸውም ሁሉን የሚያድን አምላካችን ነው። ለዘለዓለሙ ይጠብቀናል። እንሰግድለትን እናመስግነው ዘንድ እርሱ ፈጥሮናና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭፤ ድንግል ማርያም የሽቱ መኖሪያና የሕይወት ውኃ ምንጭ ናት። የማኅፀንዋ ፍሬ ሰውን ሁሉ አድኖአልና። ከእኛም እርግማንን አጠፋልን። በመካከለችንም ሆኖ በስቀሉ አስታረቀን በልዩ ትንሣኤውም ሰውን ዳንመኛ ወደ ገነት መለሰው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮፤ ንጽሕት ድንግል ማርያም የታመነች አምላክን የወለደች ናትሽ። ለሰዎች ልጆችም የምሕረት አማላጅ ናት። ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ክርስቶስ ለምኝልን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፯፤ ድንግል ማርያም በቤተመቅደስ አሰምታ ትናገር ነበር። መልአኩ ቅድስት ድንግል ሆይ ሰልምታ ይገባሻል ብሎ አክብሮ ከነገረኝ ነገር በቀር ምንም ምን ሌላ የማውቀው እንደሌለኝ እግዚአብሔር ያውቃል አለች። የማይቻለውን ቻልሽ የማይወሰነውንና ምንም ምን የሚወስነው የሌለውን ወሰንሽ። በክብር ሁሉ ላይ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ምስጋናሽ ይበዛል ክብርሽ ፍጹም ነው። የአብ ቃል ማደሪያ ሆነሻልና የክርስቲያን ወገኖች ምእመናንን የምትሰበስቢያቸውና ማሕየዊ የሚያድኑን ለሆኑ ለሥላሴ ሰጊድን (መሰገድን) የምያስተምሪላቸው ሰፊ መጋረጃ ሙሴ ያየውን የእሳት ዓምድ የተሸከምሽ አንቺ ነሽ። ይኸውም መጥቶ በማኅፀንሽ ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ሰማይና ምድር ለማይወስኑት የታመንሽ አንቺ ነሽ። ከምድር ወደሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ ብርሃንሽ ከፀሐይ ብርሃን ይበልጣል። ቅዱሳን በፍጹም ደስታ ያዩት ኮከብ ካንቺ የተወልደ ምሥራቅ አንቺ ነሽ። አንቺ ማርያም ግን ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ የሚል ቃልን ሰማሽና መጥቶ ያዳነን የፍጥረት ሁሉ ገዥ የሆነ ንጉሥን ወለድሽልን። መሐሪ ነው፣ ሰውንም ወዳጅ ነው። ስለዚህ ማርያም ሆይ የተባረክሽ ነሽ፣ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ እያልን መልአኩ ገብርኤል እንዳመሰገነሽ እናመሰግንሻለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

 

1. Blessed art thou among women, and blessed is the fruit of thy womb, O MARY the Virgin, the spotless Godbearer. From thee hath risen upon us the Sun of righteousness, and He hath drawn us near [to Him] under His wings, for He hath created us. Thou thyself alone, O our Lady, the God-bearer, art the Mother of the Light. We will magnify thee with glorifying and praising. 

2. Blessed art thou! Thou art greater than heaven, and more glorious than earth, and exalted above the conception of every mind; who is able to declare thy greatness? There is none who can be compared with thee, O MARY the Virgin. The angels magnify thee, and the Seraphim praise thee, for He Who dwelleth upon the Cherubim and Seraphim came and took up His abode in thy womb. The Lover of men hath brought us nigh unto Himself, the death that belonged to us He hath removed, and hath given unto us the Life that was His, To Him belong glory, and praise. To thee. 

3. Blessed art thou, MARY, and blessed is the Fruit of thy womb. O virgin God- bearer, the glory of [all] virgins; He Who existed before the world became incarnate of thee. The Ancient of days came forth from thy womb, He took our flesh, and gave us His Holy Spirit, and in His abundant goodness made us co-equals with Him. Thou art greater than many women who have received grace and honour, O MARY the Godbearer, thou spiritual city wherein God the Most High took up His abode. Him Who sitteth above the Cherubim an Seraphim hast thou clasped with the hand. And He, Who of His abundant goodness feedeth every being of flesh, hath taken thy breast and sucked milk there-from – He Who is our God and the Redeemer of all, He shall shepherd us for ever. Let us worship Him and praise Him, for He hath created us. To thee. 

4. MARY the Virgin is the vessel of priceless ointment, the fountain-head (or, spring) of the water of life. The Fruit of her womb hath saved all the world, and abolished the curse which lay upon us, and made peace [to be] among us. By His Cross and by His holy Resurrection hath He brought man back again into the Garden (i.e. paradise). To thee.

5. MARY, the pure Virgin, the Bearer of God, prayeth continually with compassion for the children of men. Pray thou for us to thy Son CHRIST that He may forgive us and have compassion upon us. To thee. 

6. MARY the Virgin cried out in the Sanctuary, saying, “God knoweth that I know no one and nothing more than the sound of the voice of the angle, who with hnour brought unto me glad tidings, and said unto me, ‘Peace be unto thee, O holy Virgin. Thou shalt carry Him Who cannot be carried, and shalt contain Him Who cannot be contained, and Whom nothing can contain.” Thy praise shall be abundant, O thou who art full of grace and honour, for thou didst become the dwelling-place of the Word of the Father. Thou art the tent that is spread out (i.e. pitched) and that gathereth together believing Christian folk, and teacheth them to worship the life-giving Trinity.

7. Thou art she who bore the Pillar of fire, which MOSES saw, that is to say, the Son of God, Who came and dwelt in thy womb. Thou wast the Ark of the Creator of the heavens and the earth. Thou didst carry Him in thy womb nine months. Thou hadst in trust Him Whom the heavens and the earth cannot contain. Thou wast the Ladder whereby man ascended into heaven. Thy light is greater than the light of the sun. Thou art the eastern horizon, whereout came the brilliant star which the saints looked upon with joy and gladness. The decree that God passed upon EVE was, “Thou shalt bring froth children with toil and suffering,” but thou didst hear a voice, saying, “Rejoice, O full of grace, thou hast brought forth for us the Word of the Father, the KING , the God of all creation.” He came and delivered us, for He is the Compassionate Lover of men. And because of this we praise thee, even as did the Angel GABRIEL, saying, “Blessed art thou among women, and blessed is the Fruit of thy womb; rejoice, O thou who art full of grace, God is with thee!” 

 

1. ንፅሕት ወብርህት ወቅድስት በኲሉ እንተ ሐቀፈቶ ለእግዚእ በእራኃ ወኩሉ ፍጥረት ይትፌስሑ ምስሌሃ እንዘ ይጸርሑ ወይብሉ ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት

2. ተፈሥሒ ኦ ምልእተ ፀጋ ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገስ ተፈሥሒ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡፡

3. ናስተበፅእ ዕበየኪ ኦ ግርምት ድንግል ወንፌኑ ለኪ ፍስሐ ምስለ ገብርኤል መልአክ እስመ እምፍሬ ከርስኪ ኮነ መድኀኒተ ዘመድነ ወአቅረበነ ኀበ እግዚአብሔር አቡሁ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

4. ከመ ከብካብ ዘአልቦ ጥልቀት መንፈስ ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ ወኀይለ ልዑል ፀለለኪ ኦ ማርያም አማን ወለድኪ ቃለ ወልደ አብ ዘይነብር ለዓለም መጽአ ወአድኃነነ እምኃጢአት ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት ፡፡

5. አንቲ ውእቱ ዘመድ ዘእምስርወ ዳዊት ወለድከ ለነ በሥጋ መድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋህድ ቃል ዘእም አብ ዘእምቅድመ አለም ህልው ኀብአ ርእሶ ወነስአ እምኔኪ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

6. ኮንኪ ዳግሚተ ሰማይ ዲበ ምድር ኦ ወላዲተ አምላክ ሠረቀ ለነ እምኔኪ ፀሐየ ፅድቅ ወወለድኪዮ በከመ ትንቢተ ነብያት ዘእንበለ ዘርእ ወኢሙስና፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

7. አንቲ ውእቱ ደብተራ እንተ ተሰመይክ ቅድስተ ቅዱሳን ወዉስቴታ ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኵለሄ ወዉስቴታ ጽላተ ኪዳን መሶበ ወርቅ እንተ ውስቴታ መና ኅቡዕ ዘውእቱ ወልደ እግዚአብሔር መጽአ ወሃደረ ኀበ ማርያም ድንግል ዘእንበለ ርኵስ ተሰብአ እምኔሃ ቃለ አብ ወወለደቶ ውስተ አለም ለንጉሠ ስብሐት መጽአ ወአድኀነነ ትትፌስሐ ገነት እመ በግዕ ነባቢ ወልደ አብ ዘይነብር ለዓለም መጽአ ወአድኀነነ እምኃጢአት፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

8. ተሰመይኪ እመ ለክርስቶስ ንጉሥ እምድኅረ ወለድከመ ኪያሁ ነበርኪ በድንግጊበመንክር ምስጢር ወወለድኪዮ ለአማኑኤል ወበእንተዝ አቀበኪ እንበለ ሙስና፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

9. አንቲ ውእቱ ሰዋስው ዘርእየ ያዕቆብ እግዚአብሔር ላእሌሁ እስመ ፆርኪ በከርስኪ ኅቱም ዘኢይትአወቅ እምኲለሄ ኮንኪ ለነ ሰአሊተ ኀበ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተሰብአ እምኔኪ በእንተ መድኃኒትነ ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

10. ናሁ እግዚእ ወፅአ እምኔኪ ኦ ቡርክት ጽርሕ ንፅሕት ያድህን ኲሎ ዓለመ ዘፈጠረ በዕበየ ሣህሉ ንሰብሖ ወንወድሶ እስመ ውእቱ ወመፍቀሬ ሰብእ ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

11. ተፈሥሒ ኦ ምልእተ ፀጋ ድንግል ዘእንበለ ርኲስ ልሕኲት ንፅሕት ክብረ ኩሉ ዓለም ብርሃን ዘኢትጠፍእ መቅደስ ዘኢትትነሰት በትረ ሃይማኖት ዘኢትጸንን ምስማኮሙ ለቅዱሳን ሰአሊ ለነ ኀበ ወልድኪ ኄር መድኃኒነ ይምሐረነ ወይሣሃለነ ይሥረይ ኃጢአተነ ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት ፡፡

 

፩፤ ንጽሕት ነሽ ብርህትም ነሽ። ጌታን በመኻል እጅሽ የያዝሽው ሆይ በሁሉ የተቀደሽ ነሽ። ፍጥረት ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልም ብለው እየጮኹ ካንቺ ጋር ደስ ይላቸዋል። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፪፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። ባለሟነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ። እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ።

፫፤ ግርማ ያለሽ ድንግል ሆይ ገናነትሽን እናመሰግናለን እናደንቃለን። እንደ መልአኩ ገብርኤልም ምስጋና እናቀርብልሻለን የባሕርያችን መዳን በማኅፀንሽ ፍሬ ተገኝቷልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፬፤ እንደ ሠርግ ቤት ጉድፍ የሌለብሽ ነሽ መንፈስ ቅዱስ አድሮብሻልና። የልዑል ኃይልም ጸልሎሻልና። ማርያም ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር መጥቶ ከኃጢአት ያዳነን የአብ ልጅ ቃልን በእውነት ወለድሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭፤ ከዳዊት ሥር የተገኘሽ ባሕርይ (ዘር) አንቺ ነሽ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ ወልደሽልናልና። ከአብ የተወለደ ከዓለም በፊት የነበረ አንዱ ቃል ራሱን (ባሕርዩን) ሰወረ ካንቺም የተገዥን (ሰውን) አርአያ ነሣ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮፤ አምላክን ያለርኵሰት የወለድሽው ሆይ የምድር ሁለተኛ ሰማይን ሆንሽ፣ እውነተኛ ፀሐይ ካንቺ ወጥቶልናልና። እንደነቢያት ትንቢትም ያለዘርና ያለመለወጥ ወደልሽው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፯፤ ከተለዩ የተለየች የተባልሽ የኪዳን ጽላት ያለብሽ የተሰወረ መና ያለበት የወርቅ መሶብ ያለብሽ ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ። ይኸውም መና የተባለው መጥቶ በድንግል ማርያም ማኅፀን ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የአብ ቃል በርስዋ ሰው ሆነ መጥቶ ያዳነን የባሕርይ ንጉሥን በዓለም ውስጥ የወደችው የሚናገር በግ የክርስቶስ እናቱ ገነት ደስ ይላታል ለዘለዓለም የሚኖር የአብ ልጅ እርሱ መጥቶ ከኃጢአት አድኖናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፰፤ የንጉስ ክርስቶስ እናቱን ተባልሽ እርሱን ከወለድሽ በኋላም በድንግልና ኖርሽ። ድንቅ በሆነ ምሥጢርም (ተዋህዶ) አማኑኤልን ወለድሽው ስለዚህም ባለመለወጥ አጸናሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፱፤ እግዚአብሔር በላይዋ ተቀምጦባት ያዕቆብ ያያት መሰላል አንቺ ነሽ በሁሉ በኩል የማይመረመር እርሱን ተፈትሖ በሌለበት ማኅፀንሽ ተሸክመሽዋልና። እኛን ስለማዳን ካንቺ ሰው በሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አማላጅ ሆንሽን።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲፤ የተባረክሽና ንጽሕት የሆንሽ አዳራሽ ሆይ እነሆ ጌታ የፈጠረውን ዓለም ሁሉ በይቅርታው ብዛት ያድን ዘንድ ካንቺ ወጣ (ተወለደ) ፈጽመን እናመስግነው። ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲፩፤ ያለርኩሰት ድንግል የሆንሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ የዓለም ሁሉ መክበሪያ ንጽሕት ጽዋ ነሽ። የማትጠፊ ፋና ነሽ የማትፈርሽ መቅደስ ነሽ። የቅዱሳን መደገፊያቸው (መጠጊያቸው) የማትለወጪ የሃይማኖት በትር ነሽ፣ ቸር አዳኛችን ወደ ሆነ ልጅሽ ለምኝልን ፈጽሞ ይቅር ይለንና ይምረን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

1. Pure and shining, holy and praiseworthy art thou in everything, O thou who hast clasped the Lord in her hand. All creation rejoiceth with her, and crieth out, saying, “Rejoice, O full of grace, rejoice thou, for thou hast found favour; rejoice thou, for God is with thee.”

3. We ascribe blessings to thy greatness, O awesome Virgin, and we send to thee joy with the angel GABRIEL, for the Fruit of thy womb hath become the salvation of our race, and hath brought us nigh unto God His Father. Rejoice thou.

4. As at a marriage undefiled the Holy Ghost took up His abode in thee, and the power of the Most High overshadowed thee. O MARY, verily thou hast brought forth for us the Word, the Son of the Father, Who dwelleth (or, existeth) for ever. He came and saved us from sin. Rejoice thou.

5. Shoot from the root of DAVID. Thou hast brought forth for us in the flesh our Savior JESUS CHRIST, the Onlybegotten Word, Who was of the Father, Who was hidden before the world, and hiding Himself took from thee the form (or, appearance) of a slave. Rejoice thou.

6. Thou art the Second Heaven over the earth, O spotless God-bearer. From thee hath risen upon us the Sun of righteousness, and thou didst bring Him forth, according to the prophecy of the Prophets, without seed and without defilement. Rejoice thou.

7. Thou art that Tabernacle which was called “Holy of Holies”, wherein was the Ark (Tâbôt) which was covered on all sides with plates of gold, and had therein the Table of the Covenant and the pot of gold of the hidden manna, that is to say, the Son of God. He came and dwelt with MARY, the Virgin without blemish. He was incarnate of her, and she brought forth in the world the KING of Glory. He came and delivered us. The Garden (i.e. Paradise) shall rejoice, for the Lamb that is endowed with reason, the Son of the Father, Who dwelleth for ever, hath come and delivered us from sin. Rejoice thou. 

8. Thou art called the Mother of CHRIST, the KING. After thou didst bring Him forth, thou didst continue in thy spotless virginity through a marvellous mystery. Thou didst bring forth EMMANUEL, and because of this thou didst preserve thyself undefiled. Rejoice thou.

9. Thou art the Ladder on which JACOB saw the Son of God for thou hast carried in thy sealed womb Him Who could not be touched. Thou hast become for us an intercessor with our Lord JESUS CHRIST, Who became incarnate of thee for our salvation. Rejoice thou.

10. Behold, the Lord came forth from thee, O blessed Lady, thou undefiled Bridechamber, to save the whole world which He had created in His abundant compassion and mercy. We glorify Him and we praise Him for He is the Beneficent One, the Lover of men. Rejoice thou.

11. Rejoice thou, O full of grace. Virgin unblemished, Vessel undefiled, Glory of the world, Light which shall never be extinguished, Shrine that shall never be overthrown. Staff of the Faith, thou neverfailing support of the saints, pray thou for us to thy Beneficent Son, our Redeemer, that He may have mercy upon us, and show us compassion, and forgive us our sins in His mercy for ever and ever. Amen.  

 

1. ተሰመይኪ ፍቅርተ ኦ ቡርክት እምአንስት አንቲ ዉእቱ ዳግሚት ቀመር እንተ ተሰመይ ቅድስተ ቅዱሳን ወዉስቴታ ጽላተ ኪዳን፡፲ቱ ቃላት እለ ተጽሕፋ በአፃብዒሁ ለእግዚአብሔር ቀዲሙ ዜነወነ በየዉጣ እንተ ይእቲ ቀዳሜ ስሙ ለመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ዉላጤ፡ወኮነ ዓራቄ ለሐዲስ ኪዳን፡ በዉኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሐሙ ለመሃይምናን ወለሕዝብ ዝጹሐን፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

2. ወበእንተዝ ናዐብየኪ ኩልነ፡ ኦ እግእዝእትነ ወላዲተ አምላክ ንጽሕት ኩሎ ጊዜ ንስእል ወናን ቀዐዱ ኀቤኪ፡ ከመ ንርክብ ሣህለ በኀበ መፍቀሬ ሰብእ።


3. ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሄ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይትቅዝ ይትሜሰል ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ ዘኮነ ሰብአ ዘእንበለ ፍልጠት ወኢዉላጤ፡ መለኮት ንጹሕ ዘአልቦ ሙስና ዘዕሩይ ምስለ አብ ወቦቱ አብሠራ ለንጽሕት፡ ዘእንበለ ዘርእ ኮነ ከማነ በኪነ ጥበቡ ቅዱስ፡ ዘተሰብአ እምነኪ ዘእንበለ ርኩስ፡ ደመረ መለኮቶ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

4. መቅደስ ዘይኬልልዋ ኪሩቤል እለ ሥዑላን በሥዕለ እግዚአብሔር፡ ቃል ዘተሰብአ እምኔኪ ኦ ንጽሕት ዘእንበለ ዉላጤ ኮነ ሠራዬ ኃጥአትነ ወደምሳሴ አበሳነ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

5. አንቲ ዉእቱ መሶበ ወርቅ ንፁሕ እንተ ዉስቴታ መና ኅቡእ፡ ኅብስት ዘወረደ እምሰማያት ወሀቤ ሕይወት ለኩሉ ዓለም፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

6. እንቲ ዉእቱ ተቅዋም ዘወርቅ እንተ ፆርኪ ማኅቶተ ፀዳል ኩሎ ጊዜ፡ ዘዉእቱ ብርሃኑ ለዓለም፡ ብርሃን ዘእምብርሃን ዘአልቦ ጥንት፡ አምላክ ዘእምአምላክ ዘበአማን፡ ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ዉላጤ፡ ወበምጽአቱ አብርሃ ላዕሌነ ለእለ ንነብር ዉስተ ጽልመት ወጽላሎቱ ሞት፡ ወአርአትዐ እገሪነ ዉስተ ፍኖተ ሰላም በምሥጢረ ጥበቡ ቅዱስ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

7. አንቲ ዉእቱ ማዕጠንት ዘወርቅ፡ እንተ ፆርኪ ፍሕመ እሳት፡ ብሩክ ዘነሥአ እመቅደስ ዘይሠሪ ኃጢአተ ወይደመሰስ ጌጋየ፡ ዝ ዉእቱ ዘእግዚአብሔር ቃል ዘተሰብአ እምነኪ ዘአዕረገ ለአቡሁ ርእሶ ዕጣነ ወመሥዋዕተ ሥሙረ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

8. ተፈሥሒ ኦ ማርያም ርግብ ሠናይት፡ ዘወለድኪ ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ፡ አንቲ ዉእቱ ጽጌ መዓዛ ሠናይ እንተ ሠረፀት እምሥርወ ዕሤይ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

9. በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ዘኢንበለ ተክል ወኢሠቀይዋ ማየ፡ ከማሃ አንቲኒ ኦ ወላዲተ ክርስቶስ አምላክነ ዘበአማን ዘእንበለ ዘርእ መጽአ ወአድኀነነ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

10. ለኪ ይደሉ ዘእምኩሎሙ ቅዱሳን ተስአሊ ለነ ኦ ምልእተ ጸጋ አንቲ ተዐብዪ እምሊቃነ ጳጳሳት ወፈድፋደ ትከብሪ እምነቢያት ብኪ ግርማ ራእይ ዘየዐቢ እምግርማ ሱራፌል ወኪሩቤል፡ አንቲ በአማን ምክሐ ዘመድነ ወሰአሊት ሕይወተ ለነፍሳቲነ ሰአሊ ለነ ኀበ እግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ያፅንዐነ በርትዕት ሃይማኖት ዉስተ አሚነ ዚአሁ፡ ይጸግወነ ሣህሎ ወምሕረቶ፡ ይሥረይ ኃጢአተነ በብዝኃ ምሕረቱ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

፩፤ ከሴቶሽ ይልቅ ተለይተሽ የተባረክሽ ሆይ የተወደድሽ ተባልሽ። ከተለዩ የተለየች በውስጧም የኪዳን የሕግ ጽላት ያለባት የምትባይ ሁሉተኛ ክፍል አንቺ ነሽ ኪዳንም በእግዚአብሔር ጣቶሽ የተጻፉ ዓሥሩ ቃላት ናቸው። ያለመለወጥ ካንቺ ሰው የሆነ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደገኛ ስሙን መጀመሪያ ስሙን አስቀድሞ በየውጣ ነገረን፣ ለአዲስ ኪዳንም አስታራቂ ሆነ። በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ወይም መፍሰስ ያመኑትንና ንጹሓን የሆኑትን ወገኖች አነጻቸው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፪፤ ሁል ጊዜ ንጽሕት የሆንሽ አምላክን የወለድሽ እምቤታችን ሆይ ሁላችን ስለዚህ እናገንሻለን ሰውን በሚወድ በጌታ ዘንድ ይቅርታን እናገኝ ዘንድ እንለምንሻለን ወዳንቺም እናንጋጥጣልን።

፫፤ ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረፀ በውስጥና በውጭ በወርቅ የተለበጠ ታቦት ያለመለየትና ያለመለወጥ ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይመስልልናል። ይኸውም መለውጥ የሌለበት ንጹሕ መለኮት ነው። ከአብ ጋር የተካከለ ነው ለንጽሕት በራሱ አበሠራት። በልዩ ጥበብ ያለ ወንድ ዘር እንደ እኛ ሆነ መለኮቱን አዋሕዶ ያለ ርኵሰት ባንቺ ሰው ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፬፤ በእግዚአብሔር ሥዕል የተሣሉ ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደስ አንቺ ነሽ። ንጽሕት ሆይ ያለመለወጥ ካንቺ ሰው የሆነው ቃል ኃጢአታችንን የሚያስተሠርይልንና አበሳችንን የሚደመስስልን ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭፤ የተሠወረ መና ያለብሽ የንጹሕ ወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ መናም ከሰማይ የወረደውና ለዓለም ሁሉ ሕይወትን የሚያድለው ኅብስት ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮፤ ሁል ጊዜ ብርሃንነት ያለውን ፋና የተሸከምሽ የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ ይኸውም ፋና የዓለም ብርሃን ነው። ጥንት ከሌለው ብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው። ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ ነው። ያለ መለወጥ ከአንቺ ሰው የሆነው ነው። በመምጣቱም (ሰው በመሆኑም) በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለምንኖር ለእኛ አበራን በልዩ የጥበቡ ምሥጢር በሥጋዌ የልቦናችንን እግር ወደ ሰላም መንገድ አቀናልን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፯፤ ቡሩክ ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለውን ፍሕም የተሸከምሽ የወርቅ ማዕጠንት አንቺ ነሽ ፍሕም የተባለውም ኃጢአትን የሚያስተሠርይና በደልን የሚደመስስ ነው። ይኸውም ካንቺ ሰው የሆነና ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያሳረገ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፰፤ የእግዚአብሔርን ቃል የወለድሽልን መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደሽ ይበልሽ። ከዕሴይ ሥር የወጣሽ መዐዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፱፤ ሳይተክሏትና ውሃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበረች ያለ ዘር ሰው ሆኖ ያዳነን እውነተኛ አምላክችንን ክርስቶስን የወለድሽልን ሆይ አንቺ እንደርሷ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ትለምኝልን ዘንድ ላንቺ ይገባል። አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጫለሽ ከነቢያትም ከመምህራንም ትበልጫለሽ። ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ። በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ። ለሰውነታችንም ሕይወትን የምትለምኝ ነሽ። ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኝልን ፤ እርሱን በማመን በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ ይቅርታውንና ምሕረቱን ይሰጠን ዘንድ በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

 

1. THOU wast named “Beloved Woman”, O blessed among women. Thou art the second chamber, in that thou wast called “Holiest of Holies”, and in it was the table of the Covenant and on it were the Ten Words which were written by the fingers of God. He (i.e. the Father) made known this to us first of all by “Yawtâ” (i.e. Iota), which is the first [letter] of the Name of our Redeemer JESUS CHRIST, Who became incarnate of thee without change, and became the mediator of the New Covenant, and by the shedding of His Holy Blood He purified the believers and the people who were pure. And because of this we all magnify thee, O our Lady, thou ever pure God-bearer. We beseech thee and lift our eyes to thee, so that we may find mercy and compassion with the Lover of Men.

2. [Thou art] the Tabôt (i.e. Tabernacle or, Ark) which was covered on all its sides with gold, and was made of the wood that never perisheth, and that foreshadowed for us the Word of God, Who became man without separation and change, the pure and undefiled Deity, the equal of the Father, To thee, as the pure woman, [GABRIEL] announced [Him] without seed, And He became like unto us through the might of His wisdom: He Who was incarnate of thee and He Who was spotless mingled His Divinity [without nature]. And because of this—

3. [Thou] sanctuary which the Cherubim who are fashioned in the likeness of God surround—the Word, Who was incarnate of thee, O pure woman, without change hath become the Forgiver of our sins and the Destroyer of our transgressions. And because of this

4. Thou art the holy golden pot wherein the manna is hidden, the bread which came down from heaven, the giver of life unto all the world. And because of this

5. Thou art the golden candlestick and dost hold the brilliant Light at all times, the Light which is the Light of the world, the Light of Lights which had no beginning, verily God of God, Who became incarnate of thee without change. And by His coming He shed light upon us, upon those of us who were sitting in the shadow and darkness of death, and He set our feet upon the path of peace, through the mystery of His holy wisdom. And because of this

6. Thou art the censer of gold because thou didst carry the coals of the blessed fire which He took from the sanctuary—He Who forgiveth sin an destroyeth wickedness, He Who is the Word of God, Who became incarnate of thee, and Who offered up to His Father incense and precious offerings. And because of this

7. [Thou art] the garden of delight, the garden of joy, which is planted with the trees of LEBANON, and was prepared for the saints before the world was created. [On] a great chariot, which was guarded by Cherubim and Seraphim that were fashioned out of flame of fire, one of the Seraphim visited her from heaven, and said unto her in the sanctuary, “Blessed art thou among women. The Holy Spirit shall come upon thee, and the power of the Highest shall overshadow thee, for He Who dwelleth above the Cherubim shall become the Light for all the world.”

8. Thou art the sweet-scented flower which hath sprung from the foot of JESSE. And because of this 

9. Thou art like unto the rod of AARON, which, without being planted in the ground and without watering, burst into blossom. In like manner thou, O Bearer of CHRIST, didst bring forth CHRIST our God in truth, without seed. He came and delivered us. And because of this

10. It is meet for thee, O thou who art full of grace, more than for all the saints to pray on our behalf. Thou art greater than the high-priests, and thou art more honourable than the Prophets; in thee there is majesty of appearance which is greater than the majesty of the Seraphim and Cherubim. Verily thou art the glory of our race, and thou art she who must beg for life for our souls. Pray thou then on our behalf to our Lord and Redeemer JESUS CHRIST that He may confirm us in the Right Faith, that is to say, faith in Him and the He may graciously bestow upon us His mercy and compassion, and may in His abundant mercy forgive us our sins for ever and ever. Amen.