የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መዝሙሮች

ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
አዝ ——————
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ
አዝ ———————
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
አዝ ———–
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው አቡዬ
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት
አዝ —————–
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሁኗል ጸበል እምነት
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ
አዝ ——————ገድሉ

አባ አቡነ አባ መምህርነ/፪/አባ ተክለ ሃይማኖት /፪/
እም አእላፍ/፪/ ኅሩይ እም አእላፍ ኅሩይ/፪/
አዝ…
አምላክ የጠራህ ለታላቅ ክብር
ተክለ ሃይማኖት ትጉ መምህር
ሐዋርያ ነህ በዚች በምድር/፪/
ጸሎት ምህላህ በእውነት ተሰማ
ክብርህ ታወቀ በላይ በራማ/፪/
አዝ…
ደብረ ሊባኖስ ተቀደሰች
በእጅህ መስቀል ተባረከች/፪/
ኤልሳዕ ልበልህ ቅዱስ ዮሐንስ
ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ ነህ ቅዱስ/፪/
አዝ…
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ
ጸሎትህ ሆኖናል መድኃኒትና ፈውስ/፪/
ዛሬም ስንጠራህ ቃል ኪዳንህን አምነን
ጠለ በረከትህ ለሁላችን ይሁን/፪/
አዝ…

ተክለ ሃይማኖት
ተክለ ሃይማኖት ተክለ አብ
ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅድስ
አባታችን አማልደን አስታርቀን
ከፈጣሪ ጋር አምላካችን
አዝ——————————//
በሦስት ቀን ሥላሴን ያመሰገንክ
ከጭንጫ ድንጋይ ውኃ ያፈለቅክ
አባታችን ተክለ ሃይማኖት አማልደን
በኃጢአት እንዳንሞት
አኸ… አባታችን ተክለ ሃይማኖት አማልደን
በኃጢአት እንዳንሞት
አዝ——————————//
እንደ መላእክት ክንፍ የተሰጠህ
ሰማዕት ነቢይ አንድም ካህን ነህ
መምህራችን ሃዲስ ሐዋርያ
አስተምረን የፍቅር ባለሞያ
አኸ… መምህራችን ሃዲስ ሐዋርያ
አስተምረን የፍቅር ባለሞያ
አዝ——————————//
እንደ ሱራፌል በሰማይ ሲያጥን
በምድብር ነቢይ ሆኖ ማገልገሉን
በተሰጠው ፀጋ ሲያስነሳ ሙታን
ክህነት ካንተ ዘንድ ናት
አባታችን ፍታን ከኃጢአት
አኸ… ክህነት ካንተ ዘንድ ናት
አባታችን ፍታን ከኃጢአት

ሐዋርያው መነኩሴ

ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡህ ሥላሴ/2/
ዋስ ጠበቃ ሁናት ተክልዬ(ጻድቁ) ለነፍሴ
አዝ
ዳሞት ትናገረው የአንተን ሐዋርያነት
የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት
ጸሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሐይማኖት
ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መልአክ/2/
አዝ
ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሐይማኖት
ከሰወ ልጅ ልቦና ያወጣል አጋንት
የቅዳሴው ዕጣን ሲወጣ ከዋሻው
ምድርን ይባርካል ጸሎቱ ምህላው/2/
አዝ
የኢትዮጵያን ምድር አርስከው በወንጌል
ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል
ትላንት የዘራኽው ዛሬ ለእኛ ሆኗል
አምላከ ተክልዬ ብለን ተምረናል /2/
አዝ
ከሱራፌል ተርታ ቆመህ ስታጥን
ቅዱስ ቅዱስ ብለህ ስታመሰግን
ጸሎት ትሩፋትህ ትህትና ስግደትህ
ፆምህ ከፍ አድርጎ ሰማይ አደረሰህ/2/
አዝ
ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው
መቶሎሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው
የተክልዬ ጸሎት ብዙ ነው ምስጢሩ
ስድስት ክንፍ አወጣ ቢቆረጥ
አንድ እግሩ/2/